የ7ተኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ነገ የካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ይጀምራል

የ7ተኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ነገ የካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ይጀምራል። ምዝገባው በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ መስተዳደሮች እንዲሁም በሐረሪ ክልል ሙሉ በሙሉ በዲጂታል የሚከናወን ሲሆን በአፋር ክልል ደግሞ ከዚህ በፊት በተለመደው በእጅ ወይም በማኑዋል የሚከናወን ይሆናል። በተቀሩት ክልሎች የመራጮች ምዝገባው በዲጂታል እና በማኑዋል አማራጮች ይካሄዳል።

የዲጂታል ምዝገባው በሁለት አይነት አማራጭ የሚከናወን እንደሆነ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል። አንደኛው “ምርጫዬ” የተሰኘውን የሞባይል መተግበሪያ በመጠቀም መራጮች በራሳቸው ምዝገባውን የሚያከናውኑበት ነው ሲሆን ሁለተኛው አማራጭ መራጮች አቅራቢያቸው በሚገኙ ምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት በምርጫ አስፈጻሚዎች እገዛ በታብሌት የሚያከናወን ነው።

ምርጫ ቦርድ ባወጣው የግዜ ሰሌዳ መሰረት የመራጮች ምዝገባ እስከ መጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆይ ይሆናል።