ማብራሪያ ሰጪዎች

ማብራሪያ ሰጪዎች

ማብራሪያ ሰጪዎች

የደንጣ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ለፍትህ ፓርቲ ለ7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ እንዳልሳተፍ ምርጫ ቦርድ አደናቅፎኛል ማለቱን ቦርዱ አስተባበለ

የደንጣ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ለፍትህ ፓርቲ (ደሕዴፍፓ) ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በሚካሄደው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ለመሳተፍ በክልላዊ ፖለቲካ ፓርቲነት ለመመዝገብ መሟላት ያለበትን ቅድመ ሁኔታ ቢያሟላም የእውቅና ሰርተፍኬት ባለማግኘቱ ምክንያት በምርጫው መሳተፍ እንዳልቻለ አስታወቀ። ሆኖም ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ“ምርጫ 2018 - ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” በሰጠው ምላሽ ፓርቲው የምዝገባ ጥያቄውን ያቀረበው ከመራጮች ምዝገባ 90 ቀናት በፊት ስላልሆነ እና በሕግ የተቀመጠውን ቅድመ ሁኔታ ያሟላ ባለመሆኑ ዘንድሮ በሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ላይ ሊሳተፍ እንደማይችል ገልጿል። የደሕዴፍፓ  ሊቀመንበር ኢ/ር ዳዊት ኃይሉ “ለምርጫ 2018 - ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” እንደገለጹት ፓርቲው የደንጣ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ለፍትህ ፓርቲ በሚል ስያሜ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲ የምዝገባ ጥያቄ አቅርቧል። "ልናሟላ የሚገባውን ቅድመ ዝግጅት ጨርሰን ብናቀርብም” ምርጫ ቦርድ “የእውቅና ሰርተፍኬት ያለምንም ምክንያት ሳይሰጠን በመቅረቱ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ እንዳንሳተፍ ተደርገናል" ሲሉ የፓርቲው ሊቀመንበር አክለዋል። ፓርቲው “ሕዳር 15 ቀን 2018 ዓ.ም ለቦርዱ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት የተፈቀደው እና ታኅሣሥ 18 ቀን 2018 በአዲስ አበባ ከተማ የተካሄደው የምስረታ ጉባኤ፤ የሕዝቡን ተሳትፎ እና የድጋፍ መጠኑን የሚያሳይ” እንደነበር ዳዊት...

የኢዜማው አዲሱ መሪ እዮብ መሳፍንት ስለ ፓርቲያቸው የምርጫ ዝግጅት ይናገራሉ!

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ደረጃ 299 ዕጩዎችን እንዳስመዘገበ የሚናገረው የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) በመጪው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ መንግሥት ለመመሥረት የሚያስችል ድምፅ ለማግኘት እየሠራ እንደሆነና ይህ የማይሳካ ከሆነም እንደ ሁለተኛ አማራጭ በፓርላማ “የተለየ ድምፅ የሚያስተጋባ አብላጫ መቀመጫ የያዘ ተቃዋሚ ፓርቲ ለመሆን” እንዳቀደ የፓርቲው አዲሱ መሪ እዮብ መሳፍንት አስታወቁ። ኢዜማ በቅርቡ ፓርቲውን ለ7 ዓመታት በመሪነት የመሩትን ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋንና ምክትላቸውን በአዲስ አመራር የተካ ሲሆን እዮብ መሳፍንት የፓርቲው አዲሱ መሪ ሆነው ተመርጠዋል። እዮብ የአዲሱን አመራር ዕቅድ እና የፓርቲውን የምርጫ 2018 እንቅስቃሴን አስመልክተው በተለይ “ለምርጫ 2018 - ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” እንደገለጹት ከባለፈው ምርጫ ግምገማ እና ስህተት በመነሳት እንዲሁም “እስከ ጥግ መወጠር የለብንም” ብሎ በማመን ፓርቲው የትኩረት አቅጣጫውን እንደለየ ተናግረዋል። እዮብ መሳፍንት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በዘላቂ ልማት (Sustainable Development) የዶክትሬት ዲግሪያቸውን እየሠሩ ያሉ ሲሆን፣ በሰላምና ጸጥታ እንዲሁም በፖለቲካ ሳይንስ የማስተርስ ዲግሪዎችን፣ እንዲሁም በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪ ይዘዋል። እዮብ ከ17 ዓመት በላይ በሕግ ባለሙያነት አገልግለዋል። ከፓርቲው ምስረታ ጀምሮ የአስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የነበሩት እዮብ በማከልም “ከባለፈው ስህተቶቻችን በጣም በርካታ...

የዲጂታል የመራጮች ምዝገባ ተስፋና ስጋት

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ የዕጩዎች እና የመራጮች ምዝገባ የሚያካሄድበትን የዲጂታል ሥርዓት በሀገሪቱ የምርጫ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሚተገበር አስታውቋል። ቦርዱ ይህ ሥርዓት የምርጫ ሂደቱን ለማዘመን፣ ለማቀላጠፍና የጊዜና የጉልበት ብክነትን ለማስቀረት ትልቅ ሚና እንደሚኖረው በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቆይቷል። በሌላ በኩል በዲጂታል ምዝገባ ስርዓቱ ከታገዘው  የዕጩዎች ምዝገባ ተሞክሯቸው በመነሳት  አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሂደቱ ላይ ያላቸውን ስጋት ይገልጻሉ። ለመሆኑ የዲጂታል የመራጮች ቴክኖሎጂ ምንድን ነው? በምርጫ ሂደት ውስጥ ያሉ ዋና ተዋንያን በተለይም የፖለቲካ ፓርቲዎች ስለሂደቱ ምን አይነት ግምገማ አላቸው? በተለይም ከስርዓቱ አዲስነት፣ በከፊል ከመተግበሩ፣ እንደ ኢንተርኔት ተዳራሽነት ካሉ የመሰረተ ልማት እና የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ክኅሎት (digital literacy) ክፍተቶች፣ ከሌሎች ሀገሮች ተሞክሮ እና ከሳይበር ደህንነት ጋር የተያያዙ ስጋቶችስ የትኞቹ ናቸው? የዲጂታል የመራጮች ምዝገባ ተስፋዎች እንደ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከሆነ አዲስ የሚተገበሩት የዲጂታል መመዝገቢያ ቴክኖሎጂዎች መራጮችና እጩዎች በምዝገባ ሂደት ሊያጋጥሟቸው የሚችልን መጉላላት፣ የሚያጠፉትን ጊዜና ጉልበት፣ በምዝገባ ሂደት ሊያጋጥማቸው የሚችልን ማንኛውም ተፅዕኖ ለማስቀረት ያለሙ እንደሆኑ ነው።   በተለይም አካል ጉዳተኞች (ዓይነ-ሥውራን) ራሳቸውን በራሳቸው መመዝገብ እንዲችሉ፣ መራጮች ቋሚ የመራጭነት...

የዱባዩ የምርጫ ሰነዶች እና ቁሳቁሶች ህትመት ምን ይለየዋል?

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ነሐሴ 23 ለሚያካሄደው ምርጫ የሚያገለግሉ ሰነዶች እና ቁሳቁሶች ከሀገር ውጪ ማሳተም ጀምሯል። የምርጫ ሰነዶችን ህትመት የሚያካሂደው  “አል-ጉህሬር” የተባለ በዱባይ የሚገኝ ማተሚያ ቤት ነው። የምርጫ ሰነዶች እና ቁሳቁሶች ህትመት የተጀመረው ባለፈው ታህሳስ ወር ነበር። የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ እና ምክትላቸው ውብሸት አየለ ለኬንያ፣ ኡጋንዳ፣ ማላዊ እና ዛምቢያ የምርጫ ቁሳቁሶችን እንዳተመ የተነገረለትን የዱባዩ ማተሚያ ቤትን በወቅቱ ስፍራው ድረስ በመጓዝ ጎብኝተዋል። የማተሚያ ቤቱንም ኃላፊዎችም አግኝተው አነጋግረዋቸዋል። የምርጫ መዛግብቱ እና ሰነዶቹ በአማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ትግርኛ፣ ሶማሊኛ እና አፋርኛ ቋንቋዎች እንደሚታተሙ ምርጫ ቦርድ ገልጾ ነበር። ለመራጮች ምዝገባ የሚደረገው የሰነድ ዝግጅት መጠባበቂያን ጭምር እንደሚያካትት ቦርዱ ጨምሮ ገልጿል።  ምርጫ ቦርድ የዱባዩ ህትመት የመራጮች ምዝገባን ዘመናዊ እና ተዓማኒ እንደሚያደርግ ጠቁሟል። ህትመቱ የምርጫው ሂደት አለም አቀፍ ደረጃን የጠበቀ እና አዲሱ የምርጫ ህግ ላይ የተቀመጡትን መስፈርቶች ያሟላ እንዲሆን የሚያስችል ነውም ተብሏል። ከዚህ በተጨማሪም ሊፈጠሩ የሚችሉ ስህተቶችን ለመቀነስና እና ማጭበርበርን ለማስወገድ እንደሚረዳ ተገልጿል። ህትመቱ ከዚህ ቀደም በሀገር ውስጥ ሲከናወን ከነበረው ምን እንደሚለየው ለመረዳት ዝርዝሩን ከስዕላዊ መረጃው ይመልከቱ።

የፓርላማ መቀመጫዎች ስብጥር

አሁን በስራ ላይ ያለው የኢትዮጵያ ህገ መንግስት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ቁጥር ከ550 እንዳይበልጥ ይደነግጋል ። በየአምስት ዓመት በሚካሄድ ምርጫ የሚመረጡት የምክር ቤቱ አባላት ዘጠኝ ክልሎች እና ሁለት የከተማ መስተዳድሮችን የሚወክሉ ናቸው።  ከፓርላማ መቀመጫዎች አብላጫውን ቁጥር የሚይዙት የኦሮሚያ ክልል ተመራጮች ናቸው። ኦሮሚያ 178 የተወካዮች ምክር ቤት አባላትን ያስመርጣል። በመቀመጫ ብዛት ሁለተኝነትን የያዘው የአማራ ክልል በበኩሉ በፌደራል ፓርላማ በ138 ተመራጮች ይወከላል።  ሃምሳ ስድስት ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦችን በውስጡ ያቀፈው የደቡብ ክልል የፓርላማውን ሶስተኛ ከፍተኛ ቁጥር ይዟል። ክልሉ በተወካዮች ምክር ቤት 123 አባላት አሉት። የትግራይ ክልል በፌደራሉ ፓርላማ 38 መቀመጫዎች በመያዝ በተወካዮች ብዛት በአራተኛነት ደረጃ ተቀምጧል።  ሶማሌ ክልል እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በፓርላማ ያላቸው መቀመጫ ብዛት እኩል ነው። ሁለቱም በተመሳሳይ 23 ተወካዮች በፌደራሉ የእንደራሴዎች ምክር ቤት አሏቸው። የታዳጊ ክልል የሚባሉት ቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ አፋር እና ጋምቤላ ክልሎች በድምሩ ያላቸው የፓርላማ ተወካዮች ብዛት ከሶማሌ ክልልም ሆነ ከአዲስ አበባ ያንሳል። ሶስቱ ክልሎች በድምሩ በፓርላማ የሚወከሉት በ20 ተመራጮች ነው።  እንደ አዲስ አበባ ሁሉ የከተማ አስተዳደርነት እውቅና ያለው...