ማብራሪያ ሰጪዎች
ምርጫ ቦርድ የምርጫውን ጠቅላላ ውጤት አሳወቀ፤ ብልፅግና ፓርቲ የፌዴራል መንግሥት እና የሁሉንም ክልሎችና ፌዴራል ከተሞች ማሸነፉ በይፋ ታውጇል
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ሰኔ 14 ቀን 2018 ዓ.ም. በስካይላይት ሆቴል ባዘጋጀው የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የውጤት ማሳወቂያ መርሐ ግብር ላይ አጠቃላይ የምርጫውን ፍፃሜ ይፋ አድርጓል።
ቦርዱ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ መሠረት፣ ገዢው ብልፅግና ፓርቲ ምርጫ በተካሄደባቸው የሁሉም ክልል እና የፌዴራል ከተማ ምክር ቤቶች እንዲሁም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አብላጫ ወንበሮችን በማግኘት አጠቃላይ አሸናፊነቱን በይፋ አረጋግጧል።
ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) ምርጫ ከተካሄደባቸው 501 ወንበሮች መካከል ብልፅግና ፓርቲ 438 መቀመጫዎችን ጠቅልሎ የወሰደ ሲሆን፣ ቀሪዎቹ 48 ወንበሮች በተቃዋሚ ፓርቲዎችና በግል ዕጩዎች መካከል መከፋፈላቸው ታውቋል። በተወሰኑት ላይ የድጋሚ ማጣራት ወይም ድጋሚ ምርጫ ይካኼድባቸዋል።
ቦርዱ ይፋ ባደረገው የክልል ምክር ቤቶች የመጨረሻ የውጤት ስርጭት መረጃ መሠረት፣ ብልፅግና ፓርቲ በሁሉም አካባቢዎች እጅግ ሰፊ የአብላጫ ወንበር ድምፅ አግኝቷል።
በዚህም መሠረት በኦሮሚያ ክልል ከነበሩት 528 መቀመጫዎች ውስጥ 523ቱን፣ በአማራ ክልል ከ277 መቀመጫዎች 257ቱን፣ በአፋር ክልል ከ135 መቀመጫዎች 124ቱን፣ እንዲሁም በሶማሌ ክልል ከተመዘገቡት 252 መቀመጫዎች መካከል 214ቱን ብልፅግና ፓርቲ ማሸነፍ ችሏል። በተጨማሪም በጋምቤላ ክልል ከ205 መቀመጫዎች 176ቱን፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከ165 መቀመጫዎች 145ቱን፣...
እስካሁን በይፋ የታወጁት ከፊል የምርጫ ውጤቶች ምን ይነግሩናል?
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እስከ ሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ የ7ኛውን ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ ከፊል ይፋዊ ውጤቶች በተከታታይ ማሳወቁን የቀጠለ ሲሆን፣ ምርጫ ካልተካሄደበት ከትግራይ ክልል ውጭ ባሉ በሁሉም ክልሎች እና የከተማ መስተዳድሮች የተመዘገቡ የፓርላማ እና የክልል ምክር ቤቶች አሃዛዊ መረጃዎች አጠቃላይ የምርጫውን መልክ ማሳየት ጀምረዋል።
እስካሁን ባለው ሂደት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) በጥቅሉ የ73 ወንበሮች ከፊል ውጤት የታወጀ ሲሆን፣ ገዢው ብልፅግና ፓርቲ 53 ወንበሮችን በማግኘት የ73 በመቶ የበላይነት መውሰዱ ታውቋል። ቀሪዎቹን መቀመጫዎች ተቃዋሚ ፓርቲዎች በጥምር 17 ወንበሮችን በመውሰድ ሲጋሩ፣ የግል ዕጩዎች ደግሞ 3 ወንበሮችን ማሸነፍ ችለዋል።
ለፓርላማ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ውጤት የታወጀባቸው አካባቢዎች ኦሮሚያ በ30 ወንበሮች እና አማራ በ12 ወንበሮች ሲሆኑ፣ በአማራ ክልል ተቃዋሚዎች 6 ወንበሮችን በመውሰድ ተመጣጣኝ ድርሻ አግኝተዋል።
በተጨማሪም በኦሮሚያ እና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች ተቃዋሚዎች እና የግል ዕጩዎች እያንዳንዳቸው ሦስት ሦስት ወንበሮችን የወሰዱ ሲሆን፣ ከተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) እና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) እያንዳንዳቸው አራት አራት የፓርላማ ወንበሮችን በማግኘት ቀዳሚነቱን ይዘዋል።
በክልል ምክር...
ገዢው ፓርቲ ባልተወዳደረበት የአዲስ አበባ ምርጫ ክልል 11 ዶ/ር አበባው ደሳለው ሳይመረጡ ቀሩ፤ የግል ዕጩው አቶ አበበ ገመቹ አሸነፉ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 10 ቀን 2018 ዓ.ም. ምሽቱን ይፋ ካደረጋቸው የምርጫ ክልል ውጤቶች መካከል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምርጫ ክልል 11 ውጤት አንዱ ሲሆን፣ ገዢው ብልፅግና ፓርቲ ዕጩ ባላቀረበበት በዚህ ምርጫ ክልል የትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ቅንጅት ዕጩ የነበሩት እና የፓርላማ አባሉ ዶ/ር አበባው ደሳለው ድል ሳይቀናቸው ቀርቷል።
በዚህ የምርጫ ክልል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) አብላጫ ድምፅ በማግኘት ያሸነፉት በግል የተወዳደሩት የሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አበበ ገመቹ መሆናቸውን ቦርዱ አስታውቋል።
ምርጫ ቦርድ ትናንት ይፋ ካደረጋቸው 723 ውጤቶች መካከል 5ቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውጤቶች ሲሆኑ፤ ከእነዚህም ውስጥ 2ቱ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲሁም 3ቱ ለክልል (የከተማ አስተዳደር) ምክር ቤት የቀረቡ ናቸው። ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውጤታቸው ይፋ ከተደረገባቸው መካከል አንዱ የሆነው የምርጫ ክልል 11 እጅግ በርካታ ፓርቲዎችና ዕጩዎች የተፎካከሩበት ነበር።
በዚህ የምርጫ ክልል ስር አንድ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አኢዴፓ)፣ የወላይታ ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ፣ ራያ ራዩማ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ ሕዳሴ ፓርቲ፣ ሰላም ለኢትዮጵያ ጥምረት፣ አዲስ ትውልድ ፓርቲ፣ ኢዜማ፣ ትብብር ለኢትዮጵያ...
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ የታዋቂ ፖለቲከኞች የምርጫ ውጤት ይፋ ተደረገ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ7ኛውን ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ ውጤት የማረጋገጥ ሂደቱን በመቀጠል፣ የ723 የምርጫ ክልሎችን ውጤት ማፅደቁን ዛሬ ሰኔ 10 ቀን 2018 ዓ.ም. በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቀ።
ቦርዱ በ3 ዙር ካወጃቸው ውጤቶች በተጨማሪ ዛሬ የ40 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (የፓርላማ) እና የ35 የክልሎች ምክር ቤቶችን ዝርዝር ውጤት ይፋ አድርጓል።
ቦርዱ ምሽቱን በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቀው፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በተወዳደሩባቸው የምርጫ ክልሎች አብላጫ ድምፅ ማግኘት ችለዋል።
በተጨማሪም በምርጫው በግል ዕጩነት የቀረቡት አንጋፋው ፖለቲከኛ ዶ/ር ዲማ ነጎ እና ያለተፎካካሪ የተወዳደሩት የአዲስ ትውልድ ፓርቲ (አትፓ) ፕሬዝዳንት አቶ ሰለሞን ታፈሠ በተወዳደሩባቸው የምርጫ ክልሎች ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መመረጣቸው ፀድቆላቸዋል።
በክልል ምክር ቤት ውድድር በኩል ደግሞ፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምክር ቤት ዕጩ የነበሩት የከተማዋ የሰላምና ጸጥታ ኃላፊ ሊዲያ ግርማ አብላጫ ድምፅ ማግኘታቸው የተገለጸ ሲሆን፤ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዙሪያ ምርጫ ክልል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተወዳደሩት የብልፅግና ፓርቲ ዕጩ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ ማሸነፋቸው ተረጋግጧል።
https://twitter.com/ethioelections/status/2065160538431119708/
የቦርዱ የቴክኒካል አማካሪ አርማዬ አሰፋ ቦርዱ ዛሬ...
የደንጣ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ለፍትህ ፓርቲ ለ7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ እንዳልሳተፍ ምርጫ ቦርድ አደናቅፎኛል ማለቱን ቦርዱ አስተባበለ
የደንጣ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ለፍትህ ፓርቲ (ደሕዴፍፓ) ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በሚካሄደው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ለመሳተፍ በክልላዊ ፖለቲካ ፓርቲነት ለመመዝገብ መሟላት ያለበትን ቅድመ ሁኔታ ቢያሟላም የእውቅና ሰርተፍኬት ባለማግኘቱ ምክንያት በምርጫው መሳተፍ እንዳልቻለ አስታወቀ። ሆኖም ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ“ምርጫ 2018 - ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” በሰጠው ምላሽ ፓርቲው የምዝገባ ጥያቄውን ያቀረበው ከመራጮች ምዝገባ 90 ቀናት በፊት ስላልሆነ እና በሕግ የተቀመጠውን ቅድመ ሁኔታ ያሟላ ባለመሆኑ ዘንድሮ በሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ላይ ሊሳተፍ እንደማይችል ገልጿል።
የደሕዴፍፓ ሊቀመንበር ኢ/ር ዳዊት ኃይሉ “ለምርጫ 2018 - ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” እንደገለጹት ፓርቲው የደንጣ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ለፍትህ ፓርቲ በሚል ስያሜ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲ የምዝገባ ጥያቄ አቅርቧል።
"ልናሟላ የሚገባውን ቅድመ ዝግጅት ጨርሰን ብናቀርብም” ምርጫ ቦርድ “የእውቅና ሰርተፍኬት ያለምንም ምክንያት ሳይሰጠን በመቅረቱ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ እንዳንሳተፍ ተደርገናል" ሲሉ የፓርቲው ሊቀመንበር አክለዋል።
ፓርቲው “ሕዳር 15 ቀን 2018 ዓ.ም ለቦርዱ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት የተፈቀደው እና ታኅሣሥ 18 ቀን 2018 በአዲስ አበባ ከተማ የተካሄደው የምስረታ ጉባኤ፤ የሕዝቡን ተሳትፎ እና የድጋፍ መጠኑን የሚያሳይ” እንደነበር ዳዊት...
የኢዜማው አዲሱ መሪ እዮብ መሳፍንት ስለ ፓርቲያቸው የምርጫ ዝግጅት ይናገራሉ!
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ደረጃ 299 ዕጩዎችን እንዳስመዘገበ የሚናገረው የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) በመጪው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ መንግሥት ለመመሥረት የሚያስችል ድምፅ ለማግኘት እየሠራ እንደሆነና ይህ የማይሳካ ከሆነም እንደ ሁለተኛ አማራጭ በፓርላማ “የተለየ ድምፅ የሚያስተጋባ አብላጫ መቀመጫ የያዘ ተቃዋሚ ፓርቲ ለመሆን” እንዳቀደ የፓርቲው አዲሱ መሪ እዮብ መሳፍንት አስታወቁ።
ኢዜማ በቅርቡ ፓርቲውን ለ7 ዓመታት በመሪነት የመሩትን ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋንና ምክትላቸውን በአዲስ አመራር የተካ ሲሆን እዮብ መሳፍንት የፓርቲው አዲሱ መሪ ሆነው ተመርጠዋል። እዮብ የአዲሱን አመራር ዕቅድ እና የፓርቲውን የምርጫ 2018 እንቅስቃሴን አስመልክተው በተለይ “ለምርጫ 2018 - ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” እንደገለጹት ከባለፈው ምርጫ ግምገማ እና ስህተት በመነሳት እንዲሁም “እስከ ጥግ መወጠር የለብንም” ብሎ በማመን ፓርቲው የትኩረት አቅጣጫውን እንደለየ ተናግረዋል።
እዮብ መሳፍንት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በዘላቂ ልማት (Sustainable Development) የዶክትሬት ዲግሪያቸውን እየሠሩ ያሉ ሲሆን፣ በሰላምና ጸጥታ እንዲሁም በፖለቲካ ሳይንስ የማስተርስ ዲግሪዎችን፣ እንዲሁም በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪ ይዘዋል። እዮብ ከ17 ዓመት በላይ በሕግ ባለሙያነት አገልግለዋል። ከፓርቲው ምስረታ ጀምሮ የአስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የነበሩት እዮብ በማከልም “ከባለፈው ስህተቶቻችን በጣም በርካታ...
የዲጂታል የመራጮች ምዝገባ ተስፋና ስጋት
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ የዕጩዎች እና የመራጮች ምዝገባ የሚያካሄድበትን የዲጂታል ሥርዓት በሀገሪቱ የምርጫ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሚተገበር አስታውቋል። ቦርዱ ይህ ሥርዓት የምርጫ ሂደቱን ለማዘመን፣ ለማቀላጠፍና የጊዜና የጉልበት ብክነትን ለማስቀረት ትልቅ ሚና እንደሚኖረው በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቆይቷል። በሌላ በኩል በዲጂታል ምዝገባ ስርዓቱ ከታገዘው የዕጩዎች ምዝገባ ተሞክሯቸው በመነሳት አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሂደቱ ላይ ያላቸውን ስጋት ይገልጻሉ።
ለመሆኑ የዲጂታል የመራጮች ቴክኖሎጂ ምንድን ነው? በምርጫ ሂደት ውስጥ ያሉ ዋና ተዋንያን በተለይም የፖለቲካ ፓርቲዎች ስለሂደቱ ምን አይነት ግምገማ አላቸው? በተለይም ከስርዓቱ አዲስነት፣ በከፊል ከመተግበሩ፣ እንደ ኢንተርኔት ተዳራሽነት ካሉ የመሰረተ ልማት እና የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ክኅሎት (digital literacy) ክፍተቶች፣ ከሌሎች ሀገሮች ተሞክሮ እና ከሳይበር ደህንነት ጋር የተያያዙ ስጋቶችስ የትኞቹ ናቸው?
የዲጂታል የመራጮች ምዝገባ ተስፋዎች
እንደ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከሆነ አዲስ የሚተገበሩት የዲጂታል መመዝገቢያ ቴክኖሎጂዎች መራጮችና እጩዎች በምዝገባ ሂደት ሊያጋጥሟቸው የሚችልን መጉላላት፣ የሚያጠፉትን ጊዜና ጉልበት፣ በምዝገባ ሂደት ሊያጋጥማቸው የሚችልን ማንኛውም ተፅዕኖ ለማስቀረት ያለሙ እንደሆኑ ነው።
በተለይም አካል ጉዳተኞች (ዓይነ-ሥውራን) ራሳቸውን በራሳቸው መመዝገብ እንዲችሉ፣ መራጮች ቋሚ የመራጭነት...
የዱባዩ የምርጫ ሰነዶች እና ቁሳቁሶች ህትመት ምን ይለየዋል?
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ነሐሴ 23 ለሚያካሄደው ምርጫ የሚያገለግሉ ሰነዶች እና ቁሳቁሶች ከሀገር ውጪ ማሳተም ጀምሯል። የምርጫ ሰነዶችን ህትመት የሚያካሂደው “አል-ጉህሬር” የተባለ በዱባይ የሚገኝ ማተሚያ ቤት ነው።
የምርጫ ሰነዶች እና ቁሳቁሶች ህትመት የተጀመረው ባለፈው ታህሳስ ወር ነበር። የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ እና ምክትላቸው ውብሸት አየለ ለኬንያ፣ ኡጋንዳ፣ ማላዊ እና ዛምቢያ የምርጫ ቁሳቁሶችን እንዳተመ የተነገረለትን የዱባዩ ማተሚያ ቤትን በወቅቱ ስፍራው ድረስ በመጓዝ ጎብኝተዋል። የማተሚያ ቤቱንም ኃላፊዎችም አግኝተው አነጋግረዋቸዋል።
የምርጫ መዛግብቱ እና ሰነዶቹ በአማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ትግርኛ፣ ሶማሊኛ እና አፋርኛ ቋንቋዎች እንደሚታተሙ ምርጫ ቦርድ ገልጾ ነበር። ለመራጮች ምዝገባ የሚደረገው የሰነድ ዝግጅት መጠባበቂያን ጭምር እንደሚያካትት ቦርዱ ጨምሮ ገልጿል።
ምርጫ ቦርድ የዱባዩ ህትመት የመራጮች ምዝገባን ዘመናዊ እና ተዓማኒ እንደሚያደርግ ጠቁሟል። ህትመቱ የምርጫው ሂደት አለም አቀፍ ደረጃን የጠበቀ እና አዲሱ የምርጫ ህግ ላይ የተቀመጡትን መስፈርቶች ያሟላ እንዲሆን የሚያስችል ነውም ተብሏል። ከዚህ በተጨማሪም ሊፈጠሩ የሚችሉ ስህተቶችን ለመቀነስና እና ማጭበርበርን ለማስወገድ እንደሚረዳ ተገልጿል።
ህትመቱ ከዚህ ቀደም በሀገር ውስጥ ሲከናወን ከነበረው ምን እንደሚለየው ለመረዳት ዝርዝሩን ከስዕላዊ መረጃው ይመልከቱ።
የፓርላማ መቀመጫዎች ስብጥር
አሁን በስራ ላይ ያለው የኢትዮጵያ ህገ መንግስት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ቁጥር ከ550 እንዳይበልጥ ይደነግጋል ። በየአምስት ዓመት በሚካሄድ ምርጫ የሚመረጡት የምክር ቤቱ አባላት ዘጠኝ ክልሎች እና ሁለት የከተማ መስተዳድሮችን የሚወክሉ ናቸው።
ከፓርላማ መቀመጫዎች አብላጫውን ቁጥር የሚይዙት የኦሮሚያ ክልል ተመራጮች ናቸው። ኦሮሚያ 178 የተወካዮች ምክር ቤት አባላትን ያስመርጣል። በመቀመጫ ብዛት ሁለተኝነትን የያዘው የአማራ ክልል በበኩሉ በፌደራል ፓርላማ በ138 ተመራጮች ይወከላል።
ሃምሳ ስድስት ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦችን በውስጡ ያቀፈው የደቡብ ክልል የፓርላማውን ሶስተኛ ከፍተኛ ቁጥር ይዟል። ክልሉ በተወካዮች ምክር ቤት 123 አባላት አሉት። የትግራይ ክልል በፌደራሉ ፓርላማ 38 መቀመጫዎች በመያዝ በተወካዮች ብዛት በአራተኛነት ደረጃ ተቀምጧል።
ሶማሌ ክልል እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በፓርላማ ያላቸው መቀመጫ ብዛት እኩል ነው። ሁለቱም በተመሳሳይ 23 ተወካዮች በፌደራሉ የእንደራሴዎች ምክር ቤት አሏቸው። የታዳጊ ክልል የሚባሉት ቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ አፋር እና ጋምቤላ ክልሎች በድምሩ ያላቸው የፓርላማ ተወካዮች ብዛት ከሶማሌ ክልልም ሆነ ከአዲስ አበባ ያንሳል። ሶስቱ ክልሎች በድምሩ በፓርላማ የሚወከሉት በ20 ተመራጮች ነው።
እንደ አዲስ አበባ ሁሉ የከተማ አስተዳደርነት እውቅና ያለው...








