ምርጫ 2018

ኢሰመጉ እና ኅብረት ለምርጫ አጠቃላይ የምርጫ ትዝብት ሪፖርታቸውን ይፋ አደረጉ

ግንቦት 24 ቀን 2018 የተካሄደውን 7ኛ ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ ሙሉ ሂደት የታዘቡ ሁለት አገር በቀል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አጠቃላይ የትዝብት ሪፖርታቸውን ይፋ አድርገዋል። የኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ኅብረት ለምርጫ (ምርጫ ለኅብረት) ጳጉሜን 3 ቀን 2018 እንዲሁም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) በማግስቱ ጳጉሜን 4 ቀን 2018 ይፋ ያደረጓቸው አጠቃላይ የምርጫ ትዝብት ሪፖርቶች በምርጫው ሂደት የተስተዋሉ ግድፈቶች እና ጥንካሬዎች የተዘረዘሩባቸው ናቸው። ሁለቱም ተቋማት በሪፖርቶቻቸው እንዳስገነዘቡት፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባደረጋቸው አስተዳደራዊ እና ቴክኖሎጂያዊ ማሻሻያዎች ረገድ የተመዘገቡ ጥንካሬዎች ቢኖሩም፤ ሂደቱ በመላ አገሪቱ በተንሰራፋው የፀጥታ ቀውስ እና ከድምፅ መስጫ ምሥጥራዊነት በተያያዘ በተፈፀሙ ከባድ የሕግ ጥሰቶች ጥላ ሥር የወደቀ ነበር። ሁለቱም የትዝብት ሪፖርቶች የተቀሱት የመራጮችን ነፃ ውሳኔ እና የሂደቱን ተዓማኒነት ያጠለሸው ዋነኛው ተግዳሮት በድምፅ መስጫ ምሥጢራዊ ሥፍራዎች የተፈፀሙ ጣልቃ ገብነቶች ናቸው። ኢሰመጉ ባወጣው ሪፖርት፣ “በድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ሚስጢራዊነቱ የተጠበቀ መሆን የነበረበት ቢሆንም የምርጫ አስፈፃሚዎች ወደ ድምፅ መስጫ ሳጥኖች በመግባት ሕዝቡ በነፃነት እንዳይመርጡ ማድረጋቸውን” ገልጾ፣ ድርጊቱ መራጮች በነፃ ፍላጎታቸው የመምረጥ ሕገ-መንግሥታዊ መብታቸውን የጣሰ መሆኑን ገልጿል። በተመሳሳይ መልኩ ምርጫ...