በበርካታ ሀገራት በፍጥነት የተስፋፋው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በየሀገራቱ ሊካሄዱ ቀን ተቆርጦላቸው ለነበሩ ሁነቶች መስተጓጎል ምክንያት ሆኗል። ዓለም አቀፉ የዲሞክራሲ እና የምርጫ ድጋፍ ኢንስቲትዩት (IDEA) ባለፈው ሳምንት ባወጣው መረጃ መሰረት ወረርሽኙ በ21 ሀገራት ሊካሄዱ የነበሩ ምርጫ ነክ ሁነቶች ላይ ጉልህ ተጽዕኖ በማሳደሩ ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፉ አስገድዷል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድም የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ “በመራጮች ትምህርት፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች ስልጠና እና የቁሳቁስ ስርጭትን” ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል ባለፈው ሳምንት መጨረሻ አስታውቋል። በእነዚህ ተግባራት ላይ የሚደርስ መስተጓጎል በምርጫ የጊዜ ሰሌዳው ላይ ቀጥተኛ ተጽእኖ ኧእንደሚኖረው መገለጹ ይታወሳል። ከታች የሚመለከቱት ምስላዊ መረጃ በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ የምርጫ ሁነቶቻቸውን ያራዘሙ የ10 ሀገራትን ሁኔታ ያሳያል። (ኢትዮኢሌክሽን)




