የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ የጸጥታ ሁኔታ ግምገማ 

ገዢው የብልጽግና ፓርቲ፤ ምርጫውን የተመለከቱ አቅጣጫዎች የሰፈሩበትን ሰነድ፤ ለመካከለኛ አመራሮቹ ባለፈው የካቲት ወር አጋማሽ አሰራጭቶ ነበር። ፓርቲው “ሀገራዊ የለውጥ እርምጃዎች” በሚል ርዕስ ለ40 ሺህ ገደማ ለሚሆኑ ለመካከለኛ አመራሮቹ ስልጠና ባዘጋጀው ሰነድ ላይ በኢትዮጵያ መጥቷል የሚለውን ለውጥ “ምንነት እና ስኬቶቹን” ተንትኗል። በሀገር ደረጃ ያጋጥማሉ ያላቸውን “ቀጣይ ፈተናዎች እና መሻገሪያ ስልቶችን” አመላክቷል። በዚህ ሰነድ ማገባደጃ ላይ የ2012ቱ ሃገራዊ ምርጫ ጉዳይም በ11 ገጾች ተዳስሷል። ከምርጫ ዝግጅት እስከ ድህረ ምርጫ ያሉ ሂደቶችን የተመለከተው የፓርቲው ሰነድ በምርጫ ወቅት ሊያጋጥሙ ይችላሉ ያላቸውን ተግዳሮቶች በዝርዝር አስቀምጧል። (ኢትዮኢሌክሽን)