ብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ካሉት 158 መቀመጫዎች መካከል በ24ቱ አይወዳደርም

ብልጽግና ፓርቲ ትላንት፣ መጋቢት 15፣ 2018 ይፋ ያደረገው የአዲስ አበባ ዕጩዎቹ ዝርዝር ላይ እንደተመለከተው፣ ለ7ኛውም ጠቅላላ ምርጫ ያስመዘገባቸው ዕጩዎች ብዛት 158ቱ መቀመጫዎች መካከል ለ134ቱ መሆኑ ተመላክቷል፤ ሆኖም፣ በቀሪዎቹ ሁሉም የከተማዋ የምርጫ ክልሎች ውስጥ የተወሰኑ ቁጥር ያላቸው ወኪሎችን ያላቀረበ ሲሆን፣ በድምሩ ለ24 የምክር ቤቱ መቀመጫዎች ተወዳዳሪ እጩዎችን አላስመዘገበም።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ድረገጽ ላይ እንደተመላከተው፣ በ6ተኛው ጠቅላላ ምርጫ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት መቀመጫዎች ብዛት 138 የነበረ ሲሆን፣ ብልጽግና ፓርቲም ለሁሉም መቀመጫዎች ተወዳዳሪዎችን አቅርቦ ነበር። ለ7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት መቀመጫዎች ብዛት በ20 ከፍ ብሎ 158 የደረሰ መሆኑም በቦርዱ ድረገጽ ላይ ተመላክቷል። [ምርጫ 2018 – ኢትዮጵያ ኢንሳይደር]