በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እውቅና የተሰጣቸው አገር በቀል ድርጅቶች ብዛት

ለ7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ታዛቢነት 45 እና የመራጮች ትምህርት ለመስጠት 143 የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች እውቅና ተሰጥቷቸዋል፤ የተሳታፊ ድርጅቶች ቁጥር ካለፈው ምርጫ አንፃር ቅናሽ አሳይቷል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ7ኛው ሃገራዊ ምርጫ ለመታዘብ እና የምርጫ ትምህርት መስጠት እውቅና ያገኙ ሀገር በቀል ድርጅቶችን ከወራቶች በፊት ይፋ ማድረጉ ይታወቃል። በ7ኛው ሃገራዊ ምርጫ ለመታዘብ 45 እንዲሁም የመራጮች ትምህርት ለመስጠት ደግሞ 143 ሃገር በቀል ድርጅቶች እውቅና ተሰጥቷቸዋል። ይህ አሃዝ በ6ኛው ምርጫ ከነበረው ጋር ሲነፃፀር ለመታዘብ እውቅና የተሰጣቸው በ9 ጭማሪ ሲያሳይ፤ የመራጮች ትምህርት ለመስጠት እውቅና የተሰጣቸው ደግሞ በ12 ቅናሽ አሳይቷል።

በ6ኛው ምርጫ እውቅና የተሰጣቸውን ድርጅቶች ዝርዝር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ ያደረገ ሲሆን፤ ለ7ኛው ሃገራዊ ምርጫ እውቅና የሰጣቸውን ድርጅቶች ዝርዝር እስካሁን ለህዝብ ይፋ አልተደረገም።