የምርጫ 2018 ወሳኝ ቁጥሮች

“ምርጫ 2018 – ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ከተለያዩ ሚዲያዎችና ተቋማት የሚወጡ የ7ኛው ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ ቁጥር ነክ መረጃዎች እርስ በርስ የሚጋጩና ወጥነት የሌላቸው መሆናቸውን ታዝባለች። ይህንን ክፍተት ለመሙላት የዝግጅት ክፍላችን ያደረገውን የመረጃ ማጣራት ሥራ ተከትሎ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን የመጨረሻ ይፋዊ መረጃዎች መሠረት ያደረጉ ወሳኝ ቁጥሮችን እንደሚከተለው አቀናጅተናል።

መግለጫብዛትማብራሪያ
የፖለቲካ ፓርቲዎች
ለፌዴራል ፓርላማ የሚወዳደሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች40 
ለክልል/ከተማ ምክር ቤቶች የሚወዳደሩ ፓርቲዎች41 
ለሁለቱም ምክር ቤቶች የሚወዳደሩ39 
አጠቃላይ የሚወዳደሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቁጥር426 የፖለቲካ ፓርቲዎች ዕጩ ካስመዘገቡ በኋላ ተሰርዘዋል
ድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ የታተሙ ዕጩዎች
ለፓርላማ የሚወዳደሩ ዕጩዎች ብዛት2,080481 ሴቶች እና 1,599 ወንዶች
ለክልል/ከተማ ምክር ቤት የሚወዳደሩ ዕጩዎች ብዛት8,3522,208 ሴቶች እና 6,144 ወንዶች
የግል ዕጩዎች ቁጥር8025 ለፌዴራል  እና 55 ለክልል
አጠቃላይ ዕጩዎች ብዛት10,4322,689 ሴቶች እና 7,743 ወንዶች
የምርጫ ክልሎች እና የምክር ቤት ወንበሮች
የፓርላማ መቀመጫዎች ብዛት547የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የምርጫ ክልሎች እና ወንበሮች ብዛት እኩል ነው
የክልል ምክር ቤቶች የምርጫ ክልሎች684የክልል ምክር ቤቶች የምርጫ ክልሎች እያንዳንዳቸው ከአንድ በላይ ወንበሮች አሏቸው
የክልል ምክር ቤቶች መቀመጫዎች2,916የ12 ክልሎች እና የ2 የከተማ መስተዳድሮች ምክር ቤቶች
ምርጫ የሚካሄድባቸው የፓርላማ መቀመጫዎች ብዛት50138 የትግራይ የምርጫ ክልሎች እና 8 የአማራ የምርጫ ክልሎች ምርጫ አይካሄድባቸውም
የዕጩዎች ስብጥር
አንድ ዕጩ ብቻ ያለባቸው የፓርላማ የምርጫ ክልሎች7565ቱ የብልፅግና ፓርቲ ዕጩዎች ናቸው፣ 2 የግል ዕጩዎች እና 8 የተቃዋሚ ፓርቲዎች ዕጩዎች
ብልፅግና የማይወዳደርባቸው የፓርላማ ወንበሮች48በትግራይ ክልል ምርጫ የማይካሄድባቸውን 38 ወንበሮች አይጨምርም
ብልፅግና የማይወዳደርባቸው የክልሎች ምክር ቤቶች ወንበሮች284ይህም በትግራይ ክልል ምርጫ የማይካሄድባቸውን 152 ወንበሮች አይጨምርም
የመራጮች መረጃ
የተመዘገቡ መራጮች ቁጥር50,514,15523,123,426 ሴቶች እና 27,390,729 ወንዶች
የመራጮች ትምህርት እና የምርጫ መታዘብ ዕውቅና የተሰጣቸው አገር በቀል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች
ምርጫ ለመታዘብ ዕውቅና የተሰጣቸው55 
የመራጮች ትምህርት ለመስጠት ዕውቅና የተሰጣቸው169 
ምርጫ የሚታዘቡ ዓለም ዐቀፍ ልዑካን
የአፍሪካ ኅብረት24ከ7 አገሮች የተውጣጡ ታዛቢዎች
የምስራቅ አፍሪካ በይነመንግሥታዊ ጥምረት ለልማት (IGAD)73ከ47 አገሮች የተውጣጡ ታዛቢዎች