ብልፅግና፣ ኢዜማና ትብብር ለኢትዮጵያ ከፍተኛ የእጩዎች ቁጥር ያስመዘገቡ ሦስት ፓርቲዎች ሆኑ።
“ምርጫ 2018 – ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የተመለከተው ድምር ፖለቲካ ፓርቲዎች ያስመዘገቧቸው ዕጩዎች ቁጥር እንደሚያሳየው ብልፅግና ፓርቲ 2950፣ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ፓርቲ (ኢዜማ) 1256፣ እና ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት (ትብብር ለኢትዮጵያ) 1032 ዕጩዎችን ለሕዝብ ተወካዮች እና ለክልል ምክር ቤቶች በማስመዝገብ ከፍተኛ የዕጩዎች ቁጥር ያስመዘገቡ ሦስት ፓርቲዎች ሆነዋል።
547 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎች እና 2919 የክልል ምክር ቤት መቀመጫዎች፣ በድምሩ 3466 መኖራቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መረጃ የሚያሳይ ሲሆን፣ አንድም ፓርቲ ሁሉም ምክር ቤት መቀመጫዎችን ወክሎ የሚወዳደር ዕጩ አላቀረበም። ከፍተኛ የዕጩዎች ቁጥር ያቀረበው ብልፅግና ፓርቲም ያቀረባቸው ዕጩዎች ብዛት በ516 ዕጩዎች ያንሳል። የልዩነቱን ምንጭ ዝርዝሩ እንደደረሰን እናቀርባለን።




