ኅብረቱ በ4,396 (83 በመቶዎቹ ማኑዋል እና 27 በመቶዎቹ ዲጂታል) የምርጫ ጣቢያዎች ውስጥ 522 ታዛቢዎችን ማሰማራቱን ያሳወቀ ሲሆን፣ 1,410 (32%) ጣቢያዎች ውስጥ ቢያንስ አንድ ጊዜ የምዝገባ ሂደቱ ተቋርጦ ነበር። በተጨማሪም፣ በሕግ ያልተፈቀዱ ቦታዎች ላይ የተቋቋሙ ጣቢያዎች፣ ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ ያልሆኑ ጣቢያዎች እና የምዝገባ ሰነድ ሳያቀርቡ የሚመዘገቡ መራጮች እንደገጠሙት ሪፖርት አድርጓል።
በተለይ በማኑዋል የምዝገባ ስርዓቱ፣ ኅብረቱ ከጎበኛቸው 3,953 የምርጫ ጣቢያዎች ውስጥ 502ቱ ላይ ለመመዝገብ የሚያስፈልጉ ሰነዶች ሳያቀርቡ መከናወኑን ታዝቧል።
በተጨማሪም፣ ኅብረቱ ታዛቢዎችን ካሠማራባቸው 4,396 የምርጫ ጣቢያዎች ውስጥ በ102 የማኑዋል ምዝገባ ጣቢያዎች እና 14 የዲጂታል ምዝገባ ጣቢያዎች፣ በሕግ ክልከላ በተደረገባቸው ቦታዎች (ወታደራዊ፣ ፖሊስ፣ ሃይማኖታዊ፣ ጤና ጣቢያ፣ መጠጥ ቤት ወይም ሆቴል፣ የፖለቲካ ፓርቲ ጽሕፈት ቤት እና የግል መኖሪያ ቤት) ተቋቁመው መገኘታቸውን ገልጿል። [ምርጫ 2018 – ኢትዮጵያ ኢንሳይደር]




