“ምርጫ 2018 – ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የተመለከተችው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ ያደረገው የ7ተኛው ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ የዕጩዎች ዝርዝር ሰነድ እንደሚያሳየው፣ የድሬዳዋ ከተማ ምክር ቤት ካሉት 47 የምርጫ ክልሎች ውስጥ፣ በ32ቱ ብልፅግና ብቻውን እንደሚወዳደር ተረድታለች።
የድሬዳዋ ከተማ ምክር ቤት በአጠቃላይ ካሉት 189 መቀመጫዎች ብልፅግና ፓርቲ ለ161ዱ ዕጩዎችን ያቀረበ ሲሆን፣ ከነዚህ ውስጥ 92ቱ ያለምንም ተፎካካሪ የሚወዳደሩ ናቸው። በዚህም ብልፅግና ፓርቲ 48.7 በመቶ የሚሆነውን የድሬዳዋ ከተማ ምክር ቤት ወንበሮች እንደሚቆጣጠ አስቀድሞ መገመት ተችሏል።
ከ47ቱ የምርጫ ክልሎች ውስጥ በ15ቱ፣ ስምንት ተቃዋሚ ፓርቲዎች በድምሩ 47 ዕጩዎችን ማቅረብ ሲችሉ፣ አንድ የግል ተወዳዳሪም በ02 ቀበሌ የምርጫ ክልል ይወዳደራል።
ለክልል ምክር ቤቶች በአንድ የምርጫ ክልል ከአንድ በላይ የምክር ቤት መቀመጫዎች ውድድር እንደሚደረግባቸው ይታወቃል።




