116 የምርጫ ጣቢያዎች ክልከላ በተደረገባቸው ወታደራዊ፣ ፖሊስ፣ ሃይማኖት ተቋማት እና መጠጥ ቤቶች ተቋቁመው መገኘታቸውን...
የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኅብረት ለምርጫ ትናንት ይፋ ባደረገው ሪፖርቱ በመራጮች ምዝገባ ላይ የታዩ አዎንታዊ እና አሉታዊ ኹነቶችን ገልጿል።
በዚህም ኅብረቱ ታዛቢዎችን ካሠማራባቸው 4,396 የምርጫ ጣቢያዎች ውስጥ በ102 የማኑዋል ምዝገባ ጣቢያዎች እና 14 የዲጂታል ምዝገባ ጣቢያዎች፣...
“የበጀት እጥረት” ያቀዛቀዘው የሐረር ከተማ የምርጫ ድባብ
በሐረር ከተማ የመስክ ቅኝት ለማድረግ የተንቀሳቀሰው የ“ምርጫ 2018 - ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ዘጋቢ፣ በከተማዋ የምርጫው ድባብ ካለፉት ምርጫዎች አንፃር መቀዛቀዙን አስተውሏል።
ይህንን አስመልክቶ ጥያቄ ያቀረበላቸው ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ)፣ ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት...
ዶ/ር ራሔል ባፌ ኢሶዴፓ ያስመዘገባቸው 309 ዕጩዎች መሰረዛቸውን በመቃወም ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት እና ፓርላማ...
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለኢትዮጵያ ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ (ኢሶዴፓ) በጻፈው ደብዳቤ፣ ፓርቲው ለ7ኛው ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ ያቀረባቸው ዕጩዎች ከውድድር ውጪ መደረጋቸውን አስታውቋል። ቦርዱ ይህን ውሳኔ ያስተላለፈው በፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር ዶ/ር ራሔል ባፌ አማካይነት የተመዘገቡት ዕጩዎች...
ስምረት እና ቃንጪ ሃቃ ፓርቲዎች በትግራይ ክልል የምርጫ እንቅስቃሴ አለመጀመሩ እንዳሳሰባቸው ገለጹ
ዴሞከራሲያዊ ስምረት ትግራይ (ስምረት) እና የትንሳኤ ስርዓት ቃንጪ ሃቂ (ቃንጪ ሃቂ) ፓርቲዎች የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ወቅታዊ እንቅስቃሴ እና በክልሉ የምርጫ ዝግጅት አለመጀመር እንዳሳሰባቸው ለ”ምርጫ 2018 - ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል። ቃንጪ ሃቂ ህወሓት ከጦርነቱ...
‘የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኅብረት ለምርጫ’ ለ7ኛው ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ 5 ሺሕ ታዛቢዎችን እንደሚያሰማራ...
‘የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኅብረት ለምርጫ’ ዋና ዳይሬክተር አቶ አበራ ኃይለማርያም ለ7ኛው ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ 3 ሺሕ ተቀማጭ እና 2 ሺሕ ተንቀሳቃሽ፣ በድምሩ 5 ሺሕ ታዛቢዎችን ለማሰማራት ዝግጅት ማድረጋቸውን ለ“ምርጫ 2018 - ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል።...
ምርጫ ቦርድ የመራጮች ምዝገባን ለ14 ቀናት ማራዘሙ እስከ 1.6 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ ገንዘብ እንዳስወጣው...
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመራጮች ምዝገባ ከየካቲት 28፣ 2018 ዓ.ም እስከ መጋቢት 28 ድረስ እንደሚካሄድ አቅዶት የነበረውን የጊዜ ሰሌዳ ለ14 ቀናት በማራዘሙ እስከ 1.6 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ ወጪ እንዳስወጣው ገልጿል።
“በቁጥጥር ስር የዋለ አንድም የፖለቲካ ፓርቲ ዕጩ የለም” – ምክትል ኮሚሽነር ሙሊሳ አብዲሳ
በፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ የኦፕሬሽን ዋና መምሪያ ኃላፊ የሆኑት ምክትል ኮሚሽነሩ "አንድም የታሰረ ዕጩ የለም" ይበሉ እንጂ፣ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተለያዩ ጊዜያት የዕጩዎቻቸው መታሰር እና ወከባ እንደደረሰባቸው ሲገልጹ ቆይተዋል። ለአብነትም ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት የቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዕጩ የሆኑት ወ/ት ኩሪ አሰፋ የካቲት 29 መታሰራቸውን ገልጾ በዚያው ዕለት ተፈተዋል። የትብብሩ አባል የሆነው የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) የድሬዳዋው ዕጩ አቶ ወንድወሰን ኪዳኔ መጋቢት 29 ታስረው ከቀናት በኋላ መፈታታቸውን ፓርቲው አስታውቋል። የሰላም ለኢትዮጵያ ጥምረትም በጋሞ ዞን የዲታ ምርጫ ክልል ዕጩ አቶ አብርሃም አዳሙ መታሰራቸውን በቅርቡ መግለጹ ይታወሳል።
ሰላም ለኢትዮጵያ ጥምረት የሚደርሰበት ጫና አስቸኳይ መፍትሔ ካላገኘ ራሱን ከምርጫ ሊያገል እንደሚችል አስታወቀ
ሰላም ለኢትዮጵያ ጥምረት እያካሄደ ባለው የ7ኛው ጠቅላላ ሃገራዊ የቅድመ ምርጫ ዝግጅት ላይ ገዢው ፓርቲ እና የመንግሥት የፀጥታ አካላት ከፍተኛ ጫና እና ወከባ እያሳደሩበት መሆኑን ሚያዚያ 9 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫም አሳውቆ ነበር። በዚሁ መግለጫው፣ ፓርቲው “ሕገ-ወጥና አፈናዊ አሠራር ድርጊቶች ፈፃሚ አካላት ጉዳያቸው በአስቸኳይ ተጣርቶ ለምርጫው ሂደት ካለን የጊዜ እጥረት አንፃር በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ተገቢው እርምጃ እንዲወሰድ” ጠይቆ እንደነበር ይታወሳል።
የብልጽግና ፓርቲ የፓርላማ ዕጩ የነበሩት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት በዲያቆን ዳንኤል ክብረት ተተኩ
በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ ብልጽግና ፓርቲን በመወከል በአዲስ አበባ ከተማ ለፓርላማ አባልነት ዕጩ ሆነው ቀርበው የነበሩት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ፤ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ተተኩ። ዶ/ር ሳሙኤል ከምርጫው ራሳቸውን ያገለሉት “በግል ምክንያት” እንደሆነ ለ“ምርጫ 2018 - ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።
የተጣራ የዕጩዎች ዝርዝር ሚያዚያ 23፣ 2018 ይፋ እንደሚያደርግ ምርጫ ቦርድ አሳወቀ
የካቲት 16፣ 2018 የተጠናቀቀውን የዕጩዎች ምዝገባ ተከትሎ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥቅል የዕጩዎችን መረጃ ይፋ ያደረገ ቢሆንም፣ ሙሉ የዕጩዎች ዝርዝር በቦርዱ ድረገጽ ይፋ አለመደረጉን በማስመልከት “ምርጫ 2018 - ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ለቦርዱ ተደጋጋሚ ጥያቄ ስታቀርብ ነበር። ቦርዱ ትላንት፣ ሚያዝያ 15፣ የመራጮች ምዝገባ መጠናቀቅን ለማወጅ በተዘጋጀው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ፣ “ትክክለኛ እና ጥርት ያለውን የዕጩዎች ዝርዝር” በዚህ ወር፣ ሚያዝያ 23 ይፋ እንደሚያደርግ አሳውቋል።










