የሐረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የኢዜማን ዕጩ “ካለሕግ አግባብ ከምርጫ ሰርዟል” ሲሉ የፓርቲው መሪ...

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በዛሬው ዕለት ግንቦት 7፣ 2018 ዓ.ም በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ በሐረሪ ክልል ያቀረበው ዕጩ በሐረሪ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወንጀል እና ፍትሓ ብሔር ችሎት መሠረት ከምርጫው ውጪ እንደተደረገበት አሳውቋል። የፓርቲው መሪ አቶ...

መድረክ ለምርጫ የሚወዳደረው ለተሳትፎ ያህል ብቻ እንደሆነ ሊቀ መንበሩ አቶ አምዶም ገብረሥላሴ ገለጹ

የአራት ፓርቲዎች ግንባር የሆነው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) በዘንድሮው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚወዳደረው ለተሳትፎ ያህል መሆኑን የግንባሩ ሊቀመንበር አቶ አምዶም ገብረሥላሴ ለ“ምርጫ 2018 - ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል። መድረክ ዓረና ትግራይ ለዴሞክራሲ እና ሉዓላዊነት፣ የኦሮሞ...

54 በመቶ የግል ዕጩዎች ሶማሊ ክልልን ወክለው ለክልልና ለፓርላማ ወንበሮች የሚወዳደሩ መሆናቸው ተመላከተ

ለ7ኛው ጠቅላላ አገራዊ ምርጫለፓርላማ እና ለክልል ምክር ቤቶች ከሚወዳደሩ 80 የግል ዕጩዎች መካከል፣ 43ቱ (54%) ከሱማሊ ክልል እንደሆኑ ምርጫ ቦርድ ይፋ ያደረገው ሰርተፊኬት የተሰጣቸው ዕጩዎች ዝርዝር አመላከተ። ከ43ቱ የግል ተወዳዳ ዕጩዎች 39ኙ ለክልል ምክር ቤት...

ፓርቲ የሚቀያይሩት የሐረሩ ፖለቲከኛ ተስፋሁን ምልኬ

ከሰሞኑ ደግሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኢሶዴፓ ዕጩዎች መሰረዛቸውን ካሳወቀ ቀናት ብኋላ፣ “ከምርጫው ራሴን ከዕጩነት አግልያለሁ፤ ከኢሶዴፓ አባልነት፣ አመራርነትም መልቀቄን በደብዳቤ አስገብቻለሁ” የሚል መልዕክት በቲክቶክ ገጻቸው በማስተላለፍ ከአምስተኛው የፖለቲካ ፓርቲያቸው በገዛ ፈቃዳቸው መሰናበታቸውን አሳውቀዋል።

በሲዳማ ክልል ሰባት ፓርቲዎች ሲፎካከሩ፣ በአምስት ክልሎች ብልፅግና በብቸኝነት መንግሥት መመሥረት የሚያስችል የዕጩዎች ቁጥር...

በመጪው ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. በሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ፣ ለክልል ምክር ቤቶች የሚቀርቡ ዕጩዎችን ዝርዝር “ምርጫ 2018 - ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት አጠናቅራዋለች። በዚህ የዕጩዎች መረጃ መሠረት...

‘ሥራችንን ብናስረክብም ደሞዝ እና አበል እየተከፈለን አይደለም’ በሚል የምርጫ አስፈፃሚዎች አማረሩ

በመራጮች ምዝገባ ሂደት ላይ ተሰማርተው የነበሩ የምርጫ አስፈፃሚዎች፣ ሥራቸውን በአግባቡ አጠናቀው ቢያስረክቡም የክፍያ መዘግየት ቅሬታ እንደፈጠረባቸው “ምርጫ 2018 - ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የተመለከተቻቸው የአቤቱታ ደብዳቤዎች አመላከቱ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በበኩሉ “አጠቃላይ በውሉ ያስመዘገቡት መረጃ ላይ...

ገዢው ብልፅግና ፓርቲ ለ64 የፓርላማ መቀመጫዎች ብቻውን ለምርጫ መቅረቡ ታወቀ

ገዢው ብልጽግና ፓርቲ በመጪው ግንቦት መጨረሻ በሚደረገው ምርጫ፣ በአምስት ክልሎች በሚገኙ 64 የምርጫ ክልሎች ብቻውን ለፓርላማ እንደሚወዳደር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በትላትንናው ዕለት ይፋ ያደረገው ሰነድ አመለከተ። ከእነዚህ የምርጫ ክልሎች ውስጥ አርባ ስድስቱ በኦሮሚያ፣ አስራ...

‘የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኅብረት ለምርጫ’ የመራጮች ምዝገባ ግኝት

ኅብረቱ በ4,396 (83 በመቶዎቹ ማኑዋል እና 27 በመቶዎቹ ዲጂታል) የምርጫ ጣቢያዎች ውስጥ 522 ታዛቢዎችን ማሰማራቱን ያሳወቀ ሲሆን፣ 1,410 (32%) ጣቢያዎች ውስጥ ቢያንስ አንድ ጊዜ የምዝገባ ሂደቱ ተቋርጦ ነበር። በተጨማሪም፣ በሕግ ያልተፈቀዱ ቦታዎች ላይ የተቋቋሙ ጣቢያዎች፣...

በባሕር ዳር ከተማ የምርጫ ቅስቀሳ መቀዛቀዙ ተገለጸ

ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. በሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚሳተፉ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በባሕር ዳር ከተማ የጎዳና ላይ ቅስቀሳዎችን እስካሁን አለመጀመራቸውን “ምርጫ 2018 - ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተመልክታለች። የመራጮች ምዝገባ ከተጠናቀቀ በኋላ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሰፊ እንቅስቃሴ...

አቶ ዳውድ ኢብሳ በ “ፀጥታ ስጋት” ምክንያት በዘንድሮው ምርጫ እንደማይወዳደሩ ኦነግ አስታወቀ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ፕሬዝዳንት አቶ ዳውድ ኢብሳ በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት በ7ኛው ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ በዕጩነት እንደማይወዳደሩ ድርጅቱ ገለጸ። የኦነግ የዲሲፒሊን እና ቁጥጥር ኮሚቴ ሊቀመንበር አቶ አለማየሁ ዲሮ ለ “ምርጫ 2018...