Sample Category Title
ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ውስጣዊ ክፍፍሉ ሳይቋጭ፣ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ እየተዘጋጀ መሆኑ ተገለጸ
ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ (ባልደራስ) ፓርቲ በዘንድሮው 7ኛው ጠቅላላ ሀገር አቀፍ ምርጫ “በውስጥ በነበሩ መከፋፈሎች” ውስጥ ሆኖም ለምርጫ እየተዘጋጀ መሆኑን የፓርቲው ፕሬዚዳንት አቶ አምሃ ዳኜ ለ“ምርጫ 2018 - ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገለጹ። ፕሬዚዳንቱ በውስጣዊ መከፋፈሉ ሳቢያ በበቂ ሁኔታ ዝግጅት ማድረግ ባይችሉም፣ ፓርቲው 300 የሚሆኑ ዕጩዎችን ለምርጫ ውድድር አስመዝግቧል ብለዋል።
“ከዓመት በላይ ስንካሰስ የቆየን በመሆኑ፣ ቢሯችን በላያችን ላይ በመፍረሱ፣ እንዲሁም የባንክ አካውንታችን በመዘጋቱ፣ በዚሁ ሁሉ ችግር ውስጥ ዝግጅት እያደረግን ነው” ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ ባልደራስ በውስጥ ክፍፍሉ ምክንያት፣ ከውጪ ገንዘብ ይልኩለት የነበሩት እና በቀድሞው የፓርቲው ፕሬዚዳንት የተቋቋመው የባልደራስ የሰሜን አሜሪካ ደጋፊ የሚባለው ቡድን አባላት ድጋፋቸውን ካቋረጡ ከአንድ ዓመት በላይ እንደሆናቸውም ጨምረው ገልጸዋል። አቶ አምሃ ዳኜ፣ በክፍፍሉ ሳቢያ ወደ “ሦስት ሚሊዮን የሚጠጋ ገንዘብ” በፍርድ ቤት እንደታገደባቸውም ገልጸዋል።
ይሁን እንጂ፣ የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር በቃሉ አጥናፉ፣ የክፍፍሉ መንስዔ የድርጅቱ ፕሬዚዳንት እና አፈ ጉባዔ፣ ምልዓተ ጉባኤው ያልተሟላበት የብሔራዊ ምክር ቤት ስብሰባ በማድረግ የአመራር ለውጥ በማድረጋቸው መሆኑን በመግለጽ ተችተዋል።
አቶ አምሃ ግን ልዩነቱ የተፈጠረው “በውጭ ያሉት ደጋፊዎቹ እና በሀገር ውስጥ...
በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እውቅና የተሰጣቸው አገር በቀል ድርጅቶች ብዛት
ለ7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ታዛቢነት 45 እና የመራጮች ትምህርት ለመስጠት 143 የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች እውቅና ተሰጥቷቸዋል፤ የተሳታፊ ድርጅቶች ቁጥር ካለፈው ምርጫ አንፃር ቅናሽ አሳይቷል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ7ኛው ሃገራዊ ምርጫ ለመታዘብ እና የምርጫ ትምህርት መስጠት እውቅና ያገኙ ሀገር በቀል ድርጅቶችን ከወራቶች በፊት ይፋ ማድረጉ ይታወቃል። በ7ኛው ሃገራዊ ምርጫ ለመታዘብ 45 እንዲሁም የመራጮች ትምህርት ለመስጠት ደግሞ 143 ሃገር በቀል ድርጅቶች እውቅና ተሰጥቷቸዋል። ይህ አሃዝ በ6ኛው ምርጫ ከነበረው ጋር ሲነፃፀር ለመታዘብ እውቅና የተሰጣቸው በ9 ጭማሪ ሲያሳይ፤ የመራጮች ትምህርት ለመስጠት እውቅና የተሰጣቸው ደግሞ በ12 ቅናሽ አሳይቷል።
በ6ኛው ምርጫ እውቅና የተሰጣቸውን ድርጅቶች ዝርዝር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ ያደረገ ሲሆን፤ ለ7ኛው ሃገራዊ ምርጫ እውቅና የሰጣቸውን ድርጅቶች ዝርዝር እስካሁን ለህዝብ ይፋ አልተደረገም።
የመንግሥት “ጣልቃ ገብነቱ የማይቆም ከሆነ ከ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ፉክክር እንወጣለን” – የዎሕነን ፕሬዝዳንት ዶ/ር ወልደማርያም ልሳኑ
የዎላይታ ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ (ዎሕነን) ፕሬዝዳንት ዶክተር ወልደማርያም ልሳኑ ከ“ምርጫ 2018 - ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ “በመንግሥት አካላት ምክንያት ፓርቲው የምርጫ ምልክቱን መለጠፍ እና ቅስቀሳ ማካሄድ አልቻለም” ብለዋል። “45 ሺህ የምርጫ ምልክቶችን ለጥፈን የአካባቢው የመንግሥት አካላት ወዲያውኑ አንስተውብናል” በማለት፣ “ጣልቃ ገብነቱ የማይቆም ከሆነ ከ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ፉክክር እንወጣለን” ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።
“የመንግሥት አካላት ናቸው” ያሏቸው ሰዎች የፓርቲውን ዕጩዎች ከሥራ የማባረር እና አስሮ የማዋል ነገር እየፈጸሙ እንደሆነ የገለጹት ዶ/ር ወልደማርያም፣ “በተለይም የምርጫ ምልክታችንን መለጠፍ አልቻልንም” ብለዋል። እንዲህ ዓይነት ድርጊቶች በዋናነት የሚፈጸሙት ደግሞ የፓርቲው ፕሬዝዳንት በሚወዳደሩበት ዳሞት ጋሌ ወረዳ ዋንዳራ ቦሎሶ ቀበሌ እንደሆነም አስታውቀዋል።
“መጋቢት 24/ 2018 ዓ.ም 2 መቶ 70 የምርጫ ምልክቶችን ለጥፈን ወዲያውኑ ከሥር ከሥር የመንግሥት አካላት የተለጠፉትን ምልክቶች በማንሳት በተከለከሉ ቦታዎች ላይ ማለትም ቤተ ክርስቲያንና ትምህርት ቤቶች ላይ በመለጠፍ ስማችንን የማጥፋት ሙከራ አድርገዋል” ሲሉ አክለዋል። በዚህም ምክንያት የምርጫ ምልክቱን መለጠፍ እንዳልቻለ የገለጹት የፓርቲው ፕሬዝዳንት፣ ይኼ ዓይነቱ ተግባር በዋናነት በቀበሌዎች ላይ እንደሚስተዋልና በተለይም ሙንደጃ ሳክሬ ቀበሌ፣ ምርጫ ክልል 02 ላይ...
በአማራ እና ትግራይ ክልሎች “አከራካሪ” አካባቢዎች የመራጮች ምዝገባ አልተጀመረም
ለ7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ በአማራ እና በትግራይ ክልሎች “አከራካሪ” በተባሉት አምስቱ የምርጫ ክልሎች፡- ሁመራ፣ አዲ ረመጽ፣ ጠለምት፣ ኦፍላ ኮረም እና አላማጣ የምርጫ ክልሎች ውስጥ ያሉ አካባቢዎች የመራጮች ምዝገባን ጨምሮ ምንም ዓይነት የምርጫ እንቅስቃሴ እየተካሄደ አለመሆኑን የአካባቢው የመረጃ ምንጮች ገለጹ።
ከየካቲት 28 ጀምሮ ላለፉት ሦስት ሳምንታት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ሊያካሒድ በዕቅዱ በያዘው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ በአገር አቀፍ ደረጃ እያከናወነ ባለበት ወቅት፣ እነዚህ “አከራካሪ” አካባቢዎች ላይ የምርጫ ሁኔታ ምን እንደሚመስል “ምርጫ 2018 - ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” መረጃ ለማሰባሰብ ሞክራለች። በዚህም “አከራካሪ” በሚባሉት የአማራና የትግራይ አካባቢዎች በፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) ብቻ ይደረጋል የተባለው የመጪው ምርጫ ዝግጅትን በተመለከተ ምንም ዓይነት የምርጫ እንቅስቃሴ እየተካሄደ አለመሆኑን ለመረዳት ተችሏል።
በሁመራ ከተማ የሚሰሩና ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ ባለሙያ በተለይ ለ“ምርጫ 2018 - ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” እንደገለጹት እስካሁን ድረስ ምንም ዓይነት የምርጫ እንቅስቃሴ እና የመራጮች ምዝገባ እንቅስቃሴ አልተጀመረም። ሌላዋ በሁመራ ከተማ የመንግሥት ሠራተኛ የሆኑት አስተያየት ሰጪ በበኩላቸው እስካሁን በዞኑ ውስጥ ምንም...
“ያስቀመጥኳቸው ቅድመ ሁኔታዎች ሳይሟሉ በምርጫው መወዳደር ከአጃቢነት የዘለለ ትርጉም አይሰጠኝም” – ኢሕአፓ
7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ከመካሄዱ በፊት ያስቀመጣቸው ቅድመ ሁኔታዎች እንዲፈጸሙ የጠየቀው የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)፣ መንግሥት እነዚህን ጥያቄዎች ካልመለሰ በምርጫው መሳተፉ “ከአጃቢነት የዘለለ ትርጉም የለውም” ብሎ እንደሚያምን አስታውቋል። ፓርቲው ከምርጫው በፊት እንዲፈጸሙ ካስቀመጣቸው ነጥቦች መካከል “ግጭቶች ቆመው እውነተኛ ድርድር መደረግ” እንዳለበት እና “የፖለቲካ እስረኞችና ጋዜጠኞች እንዲፈቱ” የሚሉት በዋናነት ተጠቅሰዋል።
ከ“ምርጫ 2018 - ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ጋር ቆይታ ያደረጉት የኢሕአፓ ተቀዳሚ ፕሬዝዳንት መጋቢ ብሉይ አብርሃም ኃይማኖት እና የፓርቲው ዋና ጸሐፊ ምሥጢረሥላሴ ታምራት፤ ስለ ምርጫ ዝግጅታቸውና ቀጣይ ዕቅዳቸው ማብራሪያ ሰጥተዋል። “በትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት” በተሰኘው ቅንጅት ሥር ሆኖ በአገር አቀፍ ደረጃ የሚወዳደረው ኢሕአፓ፣ በተደጋጋሚ የጠየቃቸው ጥያቄዎች እስካሁን ባለመመለሳቸው ሂደቱ ፈታኝ እንደሆነበት ገልጿል።
ፓርቲው ስድስት ቅድመ ሁኔታዎችን ያስቀመጠ ሲሆን፣ እነሱም፦ ግጭቶች ቆመው እውነተኛ ድርድር ማድረግ፣ እንደ አቶ ክርስቲያን ታደለና አቶ ዮሃንስ ቧያለው ያሉ የፖለቲካ እስረኞች እንዲሁም ጋዜጠኞች እንዲፈቱ፣ በምርጫው ላይ ዓለም አቀፍ ታዛቢ እንዲኖር፣ የድጋፍ ሰልፎችን ለማድረግ አስቻይ ሁኔታ እንዲፈጠር፣ እንዲሁም የሚዲያ ነፃነትንና የምርጫ ቦርድን ገለልተኝነት የሚያረጋግጡ ሥራዎች እንዲሠሩ የሚሉ ናቸው።
በተለይ በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች ያሉ ግጭቶች...
“የሶማሊላንዱ የባሕር በር ስምምነት ነገሮችን አበላሽቶ ኢትዮጵያ እንዳትታመን አድርጓል” – ዶ/ር አብዱልቃድር አደም
ከ“ምርጫ 2018 – ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ጋር አንድ ለአንድ ቆይታ ያደረጉት የነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) ሊቀመንበር ዶ/ር አብዱልቃድር አደም፣ ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር የተፈራረመችው የባሕር በር ስምምነት “ነገሮችን ያበላሸ ነው” ብለዋል። በሥልጣን ላይ ያለው የኢትዮጵያ መንግሥት በዓለም አቀፍ ደረጃ ቅቡልነት ካላቸው አገራት ጋር መደራደር ሲገባው፣ ገና የአገርነት ዕጣ ፈንታዋ ካልተረጋገጠው ሶማሊላንድ ጋር ስምምነት ውስጥ መግባቱ ጎረቤት አገራት ኢትዮጵያን በጥርጣሬ እንዲመለከቱ አድርጓል ሲሉ ዶ/ር አብዱልቃድር የፓርቲያቸውን ግምገማ ገልጸዋል።
በወቅቱ የኢትዮጵያ መንግሥት ከሶማሊላንድ ጋር የባሕር በር ስምምነት ሲፈራረም ፓርቲያቸው ተቃውሞ እንደነበረው ያስታወሱት ሊቀመንበሩ፤ “የባሕር በር ፍላጎቱ ጥሩ ሆኖ ሳለ፣ መንግሥት የተከተለው አካሄድ ጎረቤት አገራትን ብቻ ሳይሆን ዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ ያስከፋ በመሆኑ፣ አንድም የባሕር በር ሳናገኝ ቀርተናል” በማለት የመንግሥትን አካሄድ ተችተዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ግልጽ የሆነ ስትራቴጂ ቢከተል ኖሮ ብዙ ዕድሎች እንደነበሩ የገለጹት ሊቀመንበሩ፤ የሶማሊላንዱ ስምምነት አንካራ ላይ ሲፈርስ ሶማሊያ ‘የኢትዮጵያን የባሕር በር ጥያቄ አጤነዋለሁ’ እስከማለት ደርሳ እንደነበር ጠቁመዋል። ከዚህ በተጨማሪም ጅቡቲ የታጁራን ወደብ ኢትዮጵያ እንድትጠቀም ፈቅዳ እንደነበርም አውስተዋል።
https://twitter.com/ethioelections/status/2038613128422863144
ነእፓ ባለፈው ሳምንት ይፋ ባደረገው የምርጫ 2018...
የፖለቲካ ፓርቲዎችየዲጂታል ምዝገባ ስርዓቱ ሊያስመዘግቡ ያቀዱትን የዕጩዎች ቁጥር እንደቀነሰባቸው አስታወቁ
ከ“ምርጫ 2018 - ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ጋር ቆይታ ያደረጉ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ዕጩዎችን የማስመዘገቡ ሂደት በዲጂታል መከናወኑ እና ለመመዝገብ የብሔራዊ መታወቂያ እንደ ቅድመ ሁኔታ መቀመጡ፣ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሊያስመዘግቡ ካቀዱት የዕጩዎች ቁጥር ያነሰ ለማስመዝገብ እንዳስገደዳቸው ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት፣ ነጻነት እና እኩልነት ፓርቲ፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ፓርቲ ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ተቀዳሚ ፕሬዝዳንት መጋቢ ብሉይ አብርሃም ሃይማኖት ፓርቲያቸው አባል ሆኖ የሚወዳደርበት ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት “ዕጩዎችን በማስመዝገብ ሂደት ውስጥ ትብብሩ የገጠመው ችግር የብሔራዊ መታወቂያ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ዕጩዎቻችን የቀበሌ መታወቂያ እንዳያድሱ” መደረጋቸውም ጭምር ነው ብለዋል።
በተለይም በርካታ ዕጩዎችን እንዳስመዘገቡ በገለጹት የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች ይህ ዓይነቱ ችግር ትብብሩን በስፋት እንደገጠመው ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል። “በዚህም ምክንያት ኢሉ አባቦራ እና ደንቢ ዶሎን ጨምሮ በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች 70 ዕጩዎቻችንን ሳናስመዘግብ ቀርተናል” ቅሬታቸውን አስረድተዋል።
መጋቢ ብሉይ አብርሃም፣ ትብብሩ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በድምሩ 1,700 ዕጩዎችን ለማስመዝገብ አቅዶ አሁን ላይ በተጨባጭ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተመዘገቡት 1,223 መሆናቸውን የገለጹ ሲሆን፣ ለምርጫ ቦርድ አቤቱታ በማስገባታቸው አሁንም በምዝገባ ሂደት ላይ ያሉ 177...
ህዳሴ ፓርቲ በአዲስ አበባ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ዕጩዎችን ያቀረበ ፓርቲ ሆነ
"ምርጫ 2018 - ኢትዮጵያ ኢንሳይደር" ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት እና ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) ያቀረቧቸውን ዕጩዎች ቁጥር የተመለከተች ሲሆን፣ ህዳሴ ፓርቲ ለከተማው ምክር ቤት 155 እና ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 23 ዕጩዎችን በማቅረብ በድምሩ 178 ዕጩዎችን በማስመዝገብ ከፍተኛ ተወዳዳሪዎችን ያቀረበ ፓርቲ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል። በመከተልም፣ ብልጽግና ፓርቲ ለከተማው ምክር ቤት 134 እና ለፓርላማ 20፣ በድምሩ 154 እንዲሁም ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ለከተማው ምክር ቤት 132 እና ለፓርላማ 22፣ በድምሩ 152 ዕጩዎችን በማቅረብ በተወዳዳሪዎች ብዛት ሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃን አግኝተዋል።
ህዳሴ ፓርቲ እና የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ፓርቲ (ኢዜማ) ለ23ቱም የአዲስ አበባ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎች የሚወዳደሩ ሙሉ ዕጩዎችን ያቀረቡ ብቸኛዎቹ ፓርቲዎች ሆነዋል። ይሁን እንጂ አንድም የፖለቲካ ፓርቲ ለሁሉም የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ሙሉ 158 መቀመጫዎች የሚሆኑ ዕጩዎች አላቀረበም።
ለአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት እና የፓርላማ መቀመጫዎች ዕጩ ያቀረቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ብዛት 21 ሲሆን፣ ለአዲስ አበባ የፓርላማ ወንበሮች የሚወዳደሩ ሦስት እና ለከተማው ምክር ቤት...
ኢዜማ በ“ምርጫ 2018 – ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ዘገባ ላይ ያቀረበው ቅሬታ
“ምርጫ 2018 - ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ትላንት ሐሙስ፣ መጋቢት 16፤ “ገዢው ፓርቲ የኢዜማ መሪና ምክትላቸው ለፓርላማ በሚወዳደሩባቸው የምርጫ ክልሎች ዕጩ ተወዳዳሪዎችን ሳያቀርብ ቀረ” በሚል ርዕስ ለንባብ ላበቃው ዜና የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ያቀረበው ቅሬታ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል።
መጋቢት 16 ቀን 2018 ዓ.ም
ለኢትዮጵያን ኢንሳይደር
ጉዳዩ - በተሳሳተና የጋዜጠኝነት ስነምግባርን ባልተከተለ መልኩ አንባቢያን የተሳሳተ ግምት እንዲወስዱ በሚያደርግ መልኩ የወጣ ዘገባ እንዲታረም ስለመጠየቅ
ሚዲያው በመጋቢት 16፣ 2018 ባወጣው ዘገባ የኢዜማ መሪና ምክትል መሪ በሚወዳደሩባቸው ቦታዎች ብልፅግና እንደማይወዳደር በመግለፅ በሠራው ዘገባ ላይ ሚዲያው በፓርቲው ላይ የያዘውን የተዛባ አቋም በግልፅ የሚያሳይ እና ከአንድ ለእውነት እቆማለሁ ብሎ ከተነሳ ሚዲያ የማይጠበቅ እንዲሁም የጋዜጠኝነትን ስነምግባር ያልተከተለ ዘገባ ከፍተኛ ቅሬታ ተሰምቶናል።
አንድ ሚዲያ ስለአንድ ጉዳይ ሲዘግብ ማረጋገጥ ከሚጠበቅበት መሰረታዊ ጉዳዮች አንዱ ሙሉ መረጃ መያዝ እና ሙሉ መረጃ ለተከታዮቹ ማጋራት ጥቂቱ ነው። ነገር ግን በዚህ ዘገባ ሙሉ እና እውነተኛ መረጃ ካለመሰጠቱም በላይ ቁንፅል መረጃን በመያዝ አንባቢዎች የተሳሳተ ድምዳሜ ላይ እንዲደርሱ ሆነ ተብሎ ተሰርቷል ብለን እናምናለን። ለዚህ ማስረጃ የሚሆነው፣
በተጠቀሱት የምርጫ ክልሎች ሌሎች በርካታ...
በማዕከላዊ ጎንደር ዞንና በጎንደር ከተማ በአዘዞ ክፍለ ከተማ የምርጫ ምዝገባ ሲያስተባብሩ የነበሩ የአካባቢ ሚሊሺያዎች መገደላቸው ተሰማ
“ምርጫ 2018 - ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ትላንት መጋቢት 15፣ 2018 ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ባወጣው መግለጫ ላይ በመመሥረት ባደረገችው ማጣራት በማዕከላዊ ጎንደር ዞንና በጎንደር ከተማ በአዘዞ ክፍለ ከተማ መጋቢት 12 ቀን 2018 ዓ.ም የምርጫ ምዝገባ ሲያስተባብሩ የነበሩ ሚሊሺያዎች መገደላቸውን ከተለያዩ ምንጮች ማረጋገጥ ችላለች። ይሁንና ጥቃቱን ማን እንደፈፀመውና ምን ያህል ሚሊሻዎች እንደተገደሉ በግልጽ ማረጋገጥ አልቻለችም።
ትበብር ለኢትዮጵያ አንድነት መጋቢት 15/2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ “ድርጊቱ ፍርኃት ፈጥሮብኛል” ሲል አስታውቋል።
ትብብር ለኢትዮጵያ በመግለጫው “ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ዕጩዎችና ምርጫን ለማስተባበር የሚወጡ የመንግሥት አካላት ጭምር በተለያዩ አካባቢዎች ለከፍተኛ ሰቆቃና ሕልፈት” እየተዳረጉ መሆናቸውን ገልጽ፣ “በማዕከላዊ ጎንደር ዞን እና በጎንደር ከተማ በአዘዞ ፀዳ ክ/ከተማ ባለፈው እሑድ መጋቢት 12 ቀን የኾነውና በመራጩ፣ በዕጩዎችና በአስተባባሪዎች ላይ ያደረሰው ፍርሐት፣ ሥነልቡናዊ ጫናና ተስፋ መቁረጥ” እንደ በቂ ማሳያ ተደርጎ እንደሚወሰድ ገልጿል።
“ዕጩዎችና አባላትን አደጋ ላይ የጣሉ፣ ምርጫውን አስቻይ የማያደርጉ ኹነቶች በአስቸኳይ እንዲፈቱ” ሲልም ትብብር ለኢትዮጵያ ባወጣው መግለጫ አሳስቧል።
የፀጥታ ችግር ያለባቸው አማራ ክልል ሙሉ በሙሉ፣ በትግራይ ክልል ሙሉ በሙሉ፣ ከፊል ኦሮሚያ (ከዋና ዋና ከተሞች ወጣ ባሉ...










