Sample Category Title

ምርጫ 2018

በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ ተመራጮች ያገኙት ድምፅ መካከል እጅግ የተጋነነ ልዩነት ተስተዋለ፤ ከአንድ ሺሕ በታች እና ከግማሽ ሚሊዮን በላይ...

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ7ኛውን ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ ከፊል አሃዛዊ ዝርዝር ይፋ ያደረገ ሲሆን፣ መረጃዎቹ በተለያዩ የምርጫ ክልሎች አሸናፊ የሆኑ ተመራጮች ባገኟቸው ድምፆች መካከል እጅግ ከፍተኛ ልዩነት እንዳለ ያሳያሉ። በአንዳንድ የምርጫ ክልሎች ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የመራጮችን ድምፅ ያገኙ ተመራጮች ቢመዘገቡም፣ በሌላ በኩል ከአንድ ሺሕ እስከ አሥር ሺሕ በሚያንስ ድምፅ ያሸነፉ ዕጩዎች ግማሽ ሚሊዮን ድምፅ ካገኙት ጋር እኩል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) የመግባት ዕድል ማግኘታቸው ተስተውሏል። በዚህ ረገድ በአማራ ክልል “አዲስ ቅዳም” የምርጫ ክልል የተወዳደሩት ፈተና ባዩ ሽባባው ያገኙት አጠቃላይ ድምፅ 840 ብቻ በመሆኑ፣ በምርጫው እጅግ በጣም ዝቅተኛ ድምፅ ያገኙ ተመራጭ ሆነዋል። ፈተና ባዩ በተወዳደሩበት በዚህ የምርጫ ክልል በአጠቃላይ ድምፅ የሰጡት ሰዎች ብዛት 1,916 ብቻ መሆኑ የታወቀ ሲሆን፣ እርሳቸው ያገኙት ውጤትም የአጠቃላይ መራጮቹን 44 በመቶ ይሸፍናል። እንደ ምርጫ ቦርድ አሠራር አንድ የድምፅ መስጫ ሳጥን (ኮሮጆ) ከ1,200 እስከ 1,500 የድምፅ መስጫ ወረቀቶችን ማስተናገድ የሚችል በመሆኑ፣ ፈተና ባዩ የተወዳደሩበት የምርጫ ክልል ውስጥ በትክክል የተሰጠው አጠቃላይ ድምፅ ሁለት ኮሮጆ እንኳ የማይሞላ መሆኑን መረዳት...

ድጋሚ ቆጠራ የተደረገባቸው የምርጫ ቆጠራዎች ውጤት እስካሁን ይፋ አለመደረጉን ዕጩዎች ገለጹ፤ በሃላባ 1 የምርጫ ክልል የድምፅ ቆጠራው ለአራተኛ ጊዜ...

ሰባተኛውን ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ ተከትሎ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ድጋሚ የድምፅ ቆጠራ እንዲደረግባቸው በወሰነባቸው በርካታ የምርጫ ክልሎች ላይ ሂደቶቹ ቢጠናቀቁም፣ ቦርዱ ውጤቶቹን እስካሁን ይፋ እንዳላደረገ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ገለጹ። በአንጻሩ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሚገኘው የሃላባ 1 ምርጫ ክልል የተፈጠረውን አለመግባባት ለመፍታት የተደረጉ ተከታታይ ቆጠራዎች ባለመሳካታቸው፣ የድምፅ ቆጠራው አሁን ለአራተኛ ጊዜ በድጋሜ ሊካሄድ መሆኑን አቤቱታ አቅራቢዋ ገልጸዋል። በሃላባ 1 ምርጫ ክልል የነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) ዕጩዎችና አባላት መካከል በተፈጠረ አለመተማመንና ቆጠራው ላይ "ስህተት ተፈጥሯል" በሚል ድጋሚ ቆጠራ እንዲካሄድ ቦርዱ መወሰኑ ይታወሳል። በዚሁ ምርጫ ክልል የነእፓ ዕጩ የሆኑት ነቢሃ ሙሐመድ ለ“ምርጫ 2018 - ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” እንደገለጹት፣ ከሲዳማ ክልል 15 የሚሆኑ የምርጫ አስፈጻሚዎች ተመድበው ሂደቱ ሦስት ጊዜ ቢካሄድም አሁንም በማጭበርበር ድርጊት ላይ ቅሬታ በመኖሩ ቆጠራው ለአራተኛ ጊዜ ሊደገም ነው። ዕጩዋ ሂደቱን ሲያስረዱ “በመጀመሪያ በምርጫ ጣቢያዎች ላይ ተቆጠረ፣ በመቀጠል ሆሳዕና እንዲካሄድ ተወሰነ፣ ለሦስተኛ ጊዜ በዚያው በሆሳዕና በቦርዱ ውሳኔ ቆጠራ የተካሄደ ቢሆንም ማጭበርበር በመፈጠሩ ድጋሚ አቤቱታ ለቦርዱ አስገብቻለሁ” ብለዋል። ቦርዱ አቤቱታውን ተቀብሎ "እመለከተዋለሁ" ማለቱን የገለጹት ነቢሃ፣ በአሁኑ...

ተቃዋሚ ፓርቲዎች ለምን አያሸንፉም?

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ7ኛውን ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ የመጨረሻ ውጤት ይፋ ማድረጉን ተከትሎ፣ ብዙዎች እንደጠበቁት በአንድ ፓርቲ ፍፁም የበላይነት መጠናቀቁ ተረጋግጧል። ገዢው ብልፅግና ፓርቲ በፓርላማ 90 በመቶ ወንበሮችን እንዲሁም በክልሎች ምክር ቤቶች ደግሞ 89 በመቶ የሚሆኑትን መቀመጫዎች ጠቅልሎ ሲወስድ፣ ተቃዋሚዎችና የግል ዕጩዎች ያገኟቸው ጥቂት ወንበሮች አብዛኞቹ ገዢው ፓርቲ ዕጩ ባልቀረበባቸው አካባቢዎች የተመዘገቡ ናቸው። ይህ ኹነት በኢትዮጵያ የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት ግንባታ ጉዞ ላይ ትልቅ ጥያቄ ያስነሳል፦ ለመሆኑ በኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ለምን ማሸነፍ አይችሉም? ምርጫ 97 እንደ መታጠፊያ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የተወሰኑ የምክር ቤቶች መንበሮችን ማግኘት ይችሉ የነበረው ከ1997ቱ ምርጫ በፊት በነበሩት የመጀመሪያዎቹ የምርጫ ዓመታት ነበር። ይሁን እንጂ የሀገሪቱን የፖለቲካ ምኅዳር ሙሉ በሙሉ ያናጋውና የተቃዋሚዎችን እውነተኛ እምቅ አቅም ያሳየው ታሪካዊው የምርጫ 97 ኹነት ነበር። በወቅቱ ተቃዋሚዎች በፓርላማ ሰፊ ወንበሮችን ማሸነፍ ብቻ ሳይሆን፣ የዋና ከተማዋን የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ሙሉ በሙሉ በበላይነት ማሸነፍ ችለው ነበር። ነገር ግን ያ የእውነተኛ የፉክክር ወቅት ያጫረው ተስፋ ብዙ አልዘለቀም። መንግሥትና ተቃዋሚዎች በምርጫው ውጤት ላይ ሳይማመኑ መቅረታቸው...

ብልፅግና ፓርቲ ለተቃዋሚዎች 15 በመቶ የምርጫ ክልሎችን ትቶ ለመወዳደር ከ6 ወራት በፊት ወስኖ እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታወቁ

ገዢው ብልፅግና ፓርቲ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ወቅት ከ85 በመቶ በላይ በሆኑ የምርጫ ወንበሮች ላይ ሙሉ በሙሉ ላለመወዳደር እና ቀሪዎቹን 15 በመቶ መቀመጫዎች ለተፎካካሪ ፓርቲዎች ብቻ ለመተው ከስድስት ወራት በፊት ውሳኔ አሳልፎ እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያረጋገጡት በ6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 30ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በምርጫው ዙሪያ ባደረጉት ማብራሪያ፣ "በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ የምርጫ ታሪክ፣ ምናልባትም ዴሞክራሲ ከእኛ ወዲያ ለሚሉ ሀገራትም ቢሆኑ አድርገው በማያውቁት ልክ፣ የብልፅግና ፓርቲ ከስድስት ወራት በፊት ይህንን ምርጫ በሚመለከት በነበረን ውይይት፣ ብልፅግና ከ85 ፐርሰንት ባለፈው ወንበር አይወዳደርም" ብለዋል። https://twitter.com/ethioelections/status/2059522513437143203/ ውሳኔው በተግባር የተፈጸመው "15 ፐርሰንቱን ሙሉ በሙሉ የሚፎካከሩ ፓርቲዎች በነፃነት፣ incumbent መንግሥት በሌለበት፣ ተጭበረበረ ወይም ደግሞ መንግሥት በኃይል ወሰደው በማይሉበት ሁኔታ ብቻቸውን ይወዳደሩ" በሚል መነሻ እንደነበር አስረድተዋል። ይህንን ያልተለመደ ውሳኔ ለማሳለፍ በፓርቲው ውስጥ ጥብቅ ክርክር እንደነበር የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ "ለዲሞክራሲ ቀናይነት ሲባል የብልፅግና ፓርቲ አባላት ያኔ...

ከምርጫ ካርድ ነጠቃ እስከ ታዛቢዎች ድብደባ፤ፓርቲዎች በአንዳንድ ምርጫ ክልሎች ድጋሚ ምርጫ የጠየቁባቸው ምክንያቶች ምንድን ናቸው?

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 14 ቀን 2018 ዓ.ም. አጠቃላይ የምርጫ ውጤት ይፋ ባደረገበት ዕለት፣ በበርካታ የምርጫ ክልሎች ላይ ድጋሚ የድምፅ ቆጠራ እና ድጋሚ ምርጫ እንዲካሄድ መወሰኑን ማስታወቁ ይታወሳል። የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ንዋይ ይፋ ያደረጉትን ይህንን ውሳኔ ተከትሎ፣ “ምርጫ 2018 - ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ያነጋገረቻቸው የነፃነትና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ)፣ የሕብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ሕብር) እና የዎላይታ ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ (ዎሕነን) አመራሮች በምርጫ አስፈጻሚዎችና በአካባቢው የመንግሥት መዋቅሮች የተፈጸሙ መሠረታዊ የሕግና የሥነ ምግባር ጥሰቶች ለውሳኔው ምክንያት መሆናቸውን ገልጸዋል። የምርጫ ቦርድ መረጃ እንደሚያሳየው፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) በ10 የምርጫ ክልሎች ማለትም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል (ብርብራ፣ ገረሴ እና ዳሞት ወይዴ 2)፣ በሲዳማ ክልል (ሀገረ ሰላም እና ጩኮ)፣ በኦሮሚያ ክልል (ወልመራ፣ ክብረ መንግሥት እና አሊቦ)፣ እንዲሁም በሶማሌ ክልል (ቀላፎ) የምርጫ ክልሎች ላይ ድጋሚ የድምፅ ቆጠራ ይደረጋል። ለክልል ምክር ቤት ደግሞ በኦሮሚያ (ክብረ መንግሥት)፣ በሶማሌ (ሐርሺም)፣ በአፋር (አሚባራ) እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ (ሃላባ 1) የምርጫ ክልሎች ድጋሚ ቆጠራ ይካሄዳል። በሌላ በኩል ሂደቱ ሙሉ በሙሉ ተሰርዞ ድጋሚ ምርጫ...

“የምክር ቤት ወንበር ያገኙ ዕጩዎችን ‘አትገቡም’ ማለትም ሆነ የዲሲፕሊን እርምጃ መውሰድ በምክር ቤቱ አልተመከረበትም” ሲሉ የትብብር ፕሬዚዳንት አቶ አብርሃም...

ሰባተኛውን ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ ተከትሎ በትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ስም የምክር ቤት መቀመጫ ያሸነፉ ዕጩዎች ወደ ምክር ቤት አይገቡም መባሉን እና “እርምጃ ይወሰዳል” የሚለውን መግለጫ የትብብሩ እና የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ፕሬዚዳንት አቶ አብርሃም ጌጡ እና አንድ በውድሩ ያሸነፉ ዕጩ መቃወማቸውን ለ“ምርጫ 2018 - ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገለጹ። የትብብሩ ፕሬዚዳንት አቶ አብርሃም ጌጡ “ማንም ሰው ድምፅ አግኝቻለሁ ብሎ ምክር ቤት ቢገባ መከልከል አንችልም፤ ዕጩዎችን እንዳትገቡ ማለትም ሆነ የዲሲፕሊን እርምጃ መውሰድን በትብብሩ ምክር ቤት አልተመከረበትም” ሲሉ የውስጥ መከፋፈል መኖሩን ፍንጭ ሰጥተዋል። ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ምርጫው ከተጠናቀቀ በኋላ ግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ የዘንድሮው ምርጫ “ዴሞክራሲን አያዋልድ፣ መፍትሔም አይፈይድ” ሲል በጽኑ የኮነነ ሲሆን፣ ውጤቱ ምንም ይሁን ምን ማንኛውም ዕጩ በትብብሩ ስም ወደ ምክር ቤት ቢገባ ፍጹም ተቀባይነት እንደማይኖረው አስታውቆ ነበር። https://twitter.com/ethioelections/status/2062095246633074889 የትብብሩ ዋና ጸሐፊ ምሥጢረ ሥላሴ ታምራት በቅርቡ ከ“ምርጫ 2018 - ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ ይህንን የትብብሩን ውሳኔ ሳይቀበሉ ወደ ምክር ቤት የሚገቡ ዕጩዎችን ትብብሩ ዕውቅና እንደማይሰጥ ገልጸው፣ “በዚህ ምርጫ ለተመሠረተ ፓርላማ መግባት...

የተቃዋሚ ፓርቲዎች እና የግል ዕጩዎች ብልፅግና ፓርቲ ካልተወዳደረባቸው የምክር ቤት ወንበሮች ውጪ ምን ያህሉን አገኙ?

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ትናንት ሰኔ 14 ቀን 2018 ዓ.ም. ይፋ ባደረገው አጠቃላይ የምርጫ ውጤት መሠረት፣ ተቃዋሚ ፓርቲዎች እና የግል ተወዳዳሪዎች በድምሩ 48 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (የፓርላማ) እና 271 የክልል ምክር ቤቶች ወንበሮችን ማሸነፋቸው ታውቋል። ምንም እንኳ አጠቃላይ የምርጫው ውጤት በብዙዎች እንደተጠበቀው በገዢው ብልፅግና ፓርቲ ሰፊ የበላይነት የተጠናቀቀ ቢሆንም፣ ተቃዋሚዎች እና የግል ዕጩዎች በጠንካራ ፉክክር ለፓርላማ 4 ወንበሮችን፣ ለክልሎች ምክር ቤቶች ደግሞ 6 ወንበሮችን በቀጥታ ከብልፅግና ፓርቲ መንጠቅ ችለዋል። በምርጫው ሂደት ተቃዋሚዎች ወይም የግል ዕጩዎች ካሸነፏቸው ወንበሮች መካከል አብዛኛዎቹ ብልፅግና ፓርቲ ዕጩ ያላቀረበባቸው (ያልተወዳደረባቸው) ቦታዎች ናቸው። ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ብልፅግና ያላቀረበው በ48 የምርጫ ክልሎች ላይ የነበረ ቢሆንም፣ በአማራ ክልል በሚገኙ ስምንት የምርጫ ክልሎች ላይ በተፈጠሩ ሁኔታዎች ምርጫው ባለመካሄዱ ምክንያት 3ቱ ብልፅግና የለቀቃቸው ወንበሮች ታጥፈው፤ በአጠቃላይ ብልፅግና ዕጩ ያላቀረበባቸው የፓርላማ ወንበሮች ቁጥር ወደ 45 ዝቅ ብሏል። በተመሳሳይ ሁኔታ ለክልል ምክር ቤቶች በድምሩ ለ284 ወንበሮች ዕጩዎችን ያላቀረበ ሲሆን፣ ይህም ምርጫ ያልተካሄደባቸው አካባቢዎች ሲቀነሱ ተስተካክሎ ወደ 267 ወንበሮች ወርዷል። ነባራዊው የውጤት ስርጭት እንደሚያሳየው፣ ውጤት...

ምርጫ ቦርድ የምርጫውን ጠቅላላ ውጤት አሳወቀ፤ ብልፅግና ፓርቲ የፌዴራል መንግሥት እና የሁሉንም ክልሎችና ፌዴራል ከተሞች ማሸነፉ በይፋ ታውጇል

​የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ሰኔ 14 ቀን 2018 ዓ.ም. በስካይላይት ሆቴል ባዘጋጀው የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የውጤት ማሳወቂያ መርሐ ግብር ላይ አጠቃላይ የምርጫውን ፍፃሜ ይፋ አድርጓል። ቦርዱ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ መሠረት፣ ገዢው ብልፅግና ፓርቲ ምርጫ በተካሄደባቸው የሁሉም ክልል እና የፌዴራል ከተማ ምክር ቤቶች እንዲሁም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አብላጫ ወንበሮችን በማግኘት አጠቃላይ አሸናፊነቱን በይፋ አረጋግጧል። ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) ምርጫ ከተካሄደባቸው 501 ወንበሮች መካከል ብልፅግና ፓርቲ 438 መቀመጫዎችን ጠቅልሎ የወሰደ ሲሆን፣ ቀሪዎቹ 48 ወንበሮች በተቃዋሚ ፓርቲዎችና በግል ዕጩዎች መካከል መከፋፈላቸው ታውቋል። በተወሰኑት ላይ የድጋሚ ማጣራት ወይም ድጋሚ ምርጫ ይካኼድባቸዋል። ቦርዱ ይፋ ባደረገው የክልል ምክር ቤቶች የመጨረሻ የውጤት ስርጭት መረጃ መሠረት፣ ብልፅግና ፓርቲ በሁሉም አካባቢዎች እጅግ ሰፊ የአብላጫ ወንበር ድምፅ አግኝቷል። በዚህም መሠረት በኦሮሚያ ክልል ከነበሩት 528 መቀመጫዎች ውስጥ 523ቱን፣ በአማራ ክልል ከ277 መቀመጫዎች 257ቱን፣ በአፋር ክልል ከ135 መቀመጫዎች 124ቱን፣ እንዲሁም በሶማሌ ክልል ከተመዘገቡት 252 መቀመጫዎች መካከል 214ቱን ብልፅግና ፓርቲ ማሸነፍ ችሏል። በተጨማሪም በጋምቤላ ክልል ከ205 መቀመጫዎች 176ቱን፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከ165 መቀመጫዎች 145ቱን፣...

በዛሬው የምርጫ ውጤት እወጃ ከሁለት እስከ ስድስት አሐዝ የተራራቀ ድምፅ ያገኙ ዕጩዎች አሸናፊነታቸው ፀደቀ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ7ኛውን ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ ውጤት የማረጋገጥ ሂደቱን በመቀጠል፣ ሰኔ 12 ቀን 2018 ዓ.ም. ምሽት በስካይላይት ሆቴል በሰጠው ዕለታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ ተጨማሪ የጸደቁ ውጤቶችን ይፋ አደረገ ። ዛሬ ውጤታቸው ከተነገሩ ተመራጮች መካከል ከፍተኛውን ድምጽ ያገኙት አቶ ቲያ ሚዮ አርሳዋ ናቸው። አቶ ቲያ ሚዮ በኦሮሚያ ክልል ያቤሎ የምርጫ ክልል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የብልጽግና ፓርቲን ወክለው የተወዳደሩ ሲሆን፣ 242,357 ድምጽ በማግኘት ተመርጠዋል። በተቃራኒው እጅግ ዝቅተኛ በሆነ ድምፅ መመረጣቸው የፀደቀላቸው ዕጩ ቤዛ የማነ በርሄ ናቸው። ቤዛ የማነ በድሬዳዋ አስተዳደር፣ አዲጋ ፈለማ የክልል ምክር ቤት ምርጫ ክልል (ለ3 መቀመጫዎች በተካሄደው ምርጫ) የነጻነትና እኩልነት ፓርቲን ወክለው ተወዳድረው 43 ድምጽ በማግኘት አሸናፊ ከሆኑት ሦስት ዕጩዎች አንዱ መሆን ችለዋል። ቤዛ የማነን ብልፅግና ፓርቲ ተወዳዳሪ አላቀረበባቸውም። በዚህ የምርጫ ጣቢያ የተመዘገቡ መራጮች ቁጥር 3,002 ሲሆን፣ በምርጫ ክልሉ የተመረጡት ሌሎቹ ሁለት የብልፅግና ዕጩዎች 2,910 እና 2,857 ድምፅ ማግኘታቸው ተገልጿል። የቦርዱ የቴክኒክ አማካሪ አርማዬ አሠፋ ዛሬ በሰጡት ማብራሪያ ቦርዱ ካፀደቃቸው አዳዲስ ውጤቶች መካከል ይፋ የሆኑት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ)...

እስካሁን በይፋ የታወጁት ከፊል የምርጫ ውጤቶች ምን ይነግሩናል?

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እስከ ሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ የ7ኛውን ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ ከፊል ይፋዊ ውጤቶች በተከታታይ ማሳወቁን የቀጠለ ሲሆን፣ ምርጫ ካልተካሄደበት ከትግራይ ክልል ውጭ ባሉ በሁሉም ክልሎች እና የከተማ መስተዳድሮች የተመዘገቡ የፓርላማ እና የክልል ምክር ቤቶች አሃዛዊ መረጃዎች አጠቃላይ የምርጫውን መልክ ማሳየት ጀምረዋል። እስካሁን ባለው ሂደት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) በጥቅሉ የ73 ወንበሮች ከፊል ውጤት የታወጀ ሲሆን፣ ገዢው ብልፅግና ፓርቲ 53 ወንበሮችን በማግኘት የ73 በመቶ የበላይነት መውሰዱ ታውቋል። ቀሪዎቹን መቀመጫዎች ተቃዋሚ ፓርቲዎች በጥምር 17 ወንበሮችን በመውሰድ ሲጋሩ፣ የግል ዕጩዎች ደግሞ 3 ወንበሮችን ማሸነፍ ችለዋል። ለፓርላማ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ውጤት የታወጀባቸው አካባቢዎች ኦሮሚያ በ30 ወንበሮች እና አማራ በ12 ወንበሮች ሲሆኑ፣ በአማራ ክልል ተቃዋሚዎች 6 ወንበሮችን በመውሰድ ተመጣጣኝ ድርሻ አግኝተዋል። በተጨማሪም በኦሮሚያ እና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች ተቃዋሚዎች እና የግል ዕጩዎች እያንዳንዳቸው ሦስት ሦስት ወንበሮችን የወሰዱ ሲሆን፣ ከተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) እና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) እያንዳንዳቸው አራት አራት የፓርላማ ወንበሮችን በማግኘት ቀዳሚነቱን ይዘዋል። በክልል ምክር...