የምርጫ 2018 ዕጩዎች ስብጥር፤ በቁጥር እና በምስላዊ መግለጫ

ግንቦት 19፣ 2018 (ምርጫ 2018 - ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)፤ የ7ኛው ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ በመጪው ሰኞ፣ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ለማካሄድ የሚያስችሉ የመጨረሻ ምዕራፍ ዝግጅቶች እየተደረጉ ነው። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋዊ ሰነዶች እንደሚያመላክቱት፣ ምርጫው ከትግራይ...

ገዢው ፓርቲ የኢዜማ መሪና ምክትላቸው ለፓርላማ በሚወዳደሩባቸው የምርጫ ክልሎች ዕጩ ተወዳዳሪዎችን ሳያቀርብ ቀረ

የአዲስ አበባ ከተማ ካሉት 23 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎች መካከል ገዢው ብልጽግና ፓርቲ በሦስት የምርጫ ክልሎች ዕጩ ተወዳዳሪዎችን ሳያቀርብ ቀረ። ብልጽግና ፓርቲ ዕጩዎቹን ካላቀረበባቸው የምርጫ ክልሎች ሁለቱ፤ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) መሪ እና...

ገዢው ብልፅግና ፓርቲ ለ64 የፓርላማ መቀመጫዎች ብቻውን ለምርጫ መቅረቡ ታወቀ

ገዢው ብልጽግና ፓርቲ በመጪው ግንቦት መጨረሻ በሚደረገው ምርጫ፣ በአምስት ክልሎች በሚገኙ 64 የምርጫ ክልሎች ብቻውን ለፓርላማ እንደሚወዳደር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በትላትንናው ዕለት ይፋ ያደረገው ሰነድ አመለከተ። ከእነዚህ የምርጫ ክልሎች ውስጥ አርባ ስድስቱ በኦሮሚያ፣ አስራ...

የብልጽግና ፓርቲ የፓርላማ ዕጩ የነበሩት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት በዲያቆን ዳንኤል ክብረት ተተኩ

በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ ብልጽግና ፓርቲን በመወከል በአዲስ አበባ ከተማ ለፓርላማ አባልነት ዕጩ ሆነው ቀርበው የነበሩት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ፤ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ተተኩ። ዶ/ር ሳሙኤል ከምርጫው ራሳቸውን ያገለሉት “በግል ምክንያት” እንደሆነ ለ“ምርጫ 2018 - ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

ኢዜማ በ“ምርጫ 2018 – ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ዘገባ ላይ ያቀረበው ቅሬታ

“ምርጫ 2018 - ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ትላንት ሐሙስ፣ መጋቢት 16፤ “ገዢው ፓርቲ የኢዜማ መሪና ምክትላቸው ለፓርላማ በሚወዳደሩባቸው የምርጫ ክልሎች ዕጩ ተወዳዳሪዎችን ሳያቀርብ ቀረ” በሚል ርዕስ ለንባብ ላበቃው ዜና የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ያቀረበው ቅሬታ ሙሉ...

በሲዳማ ክልል ሰባት ፓርቲዎች ሲፎካከሩ፣ በአምስት ክልሎች ብልፅግና በብቸኝነት መንግሥት መመሥረት የሚያስችል የዕጩዎች ቁጥር...

በመጪው ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. በሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ፣ ለክልል ምክር ቤቶች የሚቀርቡ ዕጩዎችን ዝርዝር “ምርጫ 2018 - ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት አጠናቅራዋለች። በዚህ የዕጩዎች መረጃ መሠረት...

በ7ተኛው ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ ስንት የተቃዋሚ ፓርቲ ወኪሎች ወይም የግል ተወዳዳሪዎች ፓርላማ ሊገቡ ይችላሉ?

(ምርጫ 2018 - ኢትዮጵያ ኢንሳይደር) ነገ፣ ግንቦት 24፣ 2018 በሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ፣ ለፓርላማ ምርጫ የሚካሄድባቸው የፓርላማ ወንበሮች 501 መሆናቸው ታውቋል፤ ይህም የሆነው የትግራይ 38 እና የአማራ 8 ወንበሮች ምርጫ ስለማይካሄድባቸው ነው። ብልፅግና ፓርቲ...

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የቅድመ ምርጫ 2018 አዘጋገብ ምን ይመስላል?

መጋቢት 4፣ 2018 — “ምርጫ 2018 - ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን (ኢቲቪ) ከጥር 16 እስከ የካቲት 15 ቀን 2018 ዓ.ም ባለው የአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በምሽት ሁለት ሰዓት ዜናዎቹ ያቀረባቸውን ዘገባዎች መርምሯል። ዳሰሳው ትኩረት ያደረገው...

ዶ/ር ራሔል ባፌ ኢሶዴፓ ያስመዘገባቸው 309 ዕጩዎች መሰረዛቸውን በመቃወም ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት እና ፓርላማ...

​የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለኢትዮጵያ ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ (ኢሶዴፓ) በጻፈው ደብዳቤ፣ ፓርቲው ለ7ኛው ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ ያቀረባቸው ዕጩዎች ከውድድር ውጪ መደረጋቸውን አስታውቋል። ቦርዱ ይህን ውሳኔ ያስተላለፈው በፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር ዶ/ር ራሔል ባፌ አማካይነት የተመዘገቡት ዕጩዎች...

አቶ ዳውድ ኢብሳ በ “ፀጥታ ስጋት” ምክንያት በዘንድሮው ምርጫ እንደማይወዳደሩ ኦነግ አስታወቀ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ፕሬዝዳንት አቶ ዳውድ ኢብሳ በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት በ7ኛው ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ በዕጩነት እንደማይወዳደሩ ድርጅቱ ገለጸ። የኦነግ የዲሲፒሊን እና ቁጥጥር ኮሚቴ ሊቀመንበር አቶ አለማየሁ ዲሮ ለ “ምርጫ 2018...