“ገዢው ፓርቲ የመንግሥት ልማትን ለምርጫ ቅስቀሳ ተጠቅሞበታል” ሲል ኢዜማ ወቀሰ

ሰኞ ግንቦት 24 ቀን የተካሄደውን 7ኛውን ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ ተከትሎ፣ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ዛሬ አርብ ግንቦት 28 ቀን 2018 ዓ.ም. በሰጠው መግለጫ ምርጫው በሰላም መጠናቀቁ በበጎ የሚነሳ ቢሆንም፣ በገዢው ፓርቲ መዋቅራዊ ተፅዕኖዎች፣ በምርጫ...

ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት የጥምረቱ የምርጫ ጉዳዮች ኃላፊ ሰጥተውታል የተባለውን መግለጫ “በተግባርም በአስተዋፅዖም የማናውቀው ግለሰብ”...

ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት (ትብብር) የተሰኘው የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥምረት ዛሬ አርብ ግንቦት 28 ቀን 2018 ዓ.ም. በማኅበራዊ ድረገጹ ባወጣው መግለጫ, “በትብብሩ ስም የተሰጠ እና የድርጅቱን ይፋዊ አቋም የማይወክል፣ እንዲያውም ከተቋቋምንበት ዓላማ በተፃራሪ የቆመ መግለጫ በሚዲያ ተሰራጭቷል”...

የተፈናቀሉበት አካባቢ ያሉ ዕጩዎችን ለመምረጥ እንደተገደዱ የደብረ ብርሃን ተፈናቃዮች ገለጹ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአገር ውስጥ ተፈናቃዮች (IDPs) እና በሚሊተሪ ካምፖች ውስጥ በመጪው ሰኔ 2 ቀን 2018 ዓ.ም. ልዩ የምርጫ ድምፅ አሰጣጥ እንደሚካሄድ በገለጸ ማግስት፣ በደብረ ብርሃን መጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ ተፈናቃዮች በሂደቱ ላይ ያላቸውን ጠንካራ...

የምርጫው ይፋዊ ውጤት ከሚታወጅበት ሁለት ቀን አስቀድሞ ልዩ የምርጫ መርሐ-ግብር እንደሚኖር ቦርዱ አስታወቀ

ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ባለፈው ሰኞ ተካሄዶ መጠናቀቁ ቢገለጽም፤ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች እና የመከላከያ ሰራዊት አባላት ግን ድምጻቸውን የሚሰጡት ገና በሚቀጥለው ሳምንት እንደሆነ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገልጿል። ቦርዱ የምርጫውን የመጨረሻ ይፋዊ ውጤት ይገልጻል ተብሎ ከሚጠበቅበት...

የአፍሪካ ኅብረት እና ኢጋድ በከፊል ኢትዮጵያ ምርጫ አለመካሄዱ በአካታችነቱ ላይ ክፍተት መፍጠሩን ገለጹ

ከሁለት ቀናት በፊት ግንቦት 24 ቀን የተከናወነውን 7ኛውን ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ አስመልክቶ፣ የአፍሪካ ኅብረት (AU) እና የምሥራቅ አፍሪካ በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) የታዛቢዎች ቡድን ዛሬ ግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም. የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። መግለጫውን...

በ130 ምርጫ ጣቢያዎች የመራጮች መዝገብ ላይ ያልተገኙ እና ካርድ ያልያዙ መራጮች እንዲመርጡ መደረጋቸውን ኅብረት...

ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የተከናወነውን 7ኛውን ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ አስመልክቶ፣ የኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ኅብረት ለምርጫ (ኅብረት ለምርጫ) ዛሬ ረቡዕ ግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም. ባወጣው የመጀመሪያ ደረጃ የትዝብት ሪፖርት፤ በድምፅ አሰጣጥ እና በቆጠራ...

በቁጫ ምርጫ ክልል የተካሄደው 7ኛው አገራዊ ምርጫ “ተጭበርብሯል” ሲል ቁሕዴፓ አስታወቀ

ከሁለት ቀናት በፊት ግንቦት 24 ቀን በተከናወነው 7ኛው ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ ላይ በቁጫ ምርጫ ክልል የተካሄደው የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ፍጹም ተዓማኒነት የሌለው እና “የተጭበረበረ” ነው ሲል የቁጫ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቁሕዴፓ) በጽኑ ወቀሰ። ፓርቲው ዛሬ ረቡዕ...

ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት አባላቱ ቢመረጡም እንኳን በጥምረቱ ስም ወደ ምክር ቤት እንዳይገቡ አሳሰበ

ከትላንት በስቲያ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የተከናወነውን 7ኛውን ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ ተከትሎ፣ ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት የተሰኘው የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥምረት ባወጣው መግለጫ፣ የዘንድሮው ምርጫ “ዴሞክራሲን አያዋልድም፣ መፍትሔም አይፈይድም” ሲል በጽኑ ወቀሰ። ጥምረቱ ዛሬ፣ ረቡዕ፣ ግንቦት 26...

የአውሮፓ ኅብረት አገራት 7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ “መካሄዱን” እንቀበለዋለን አሉ፤ ምርጫ ያልተካሄደባቸው የምርጫ ክልሎችም “ይህን...

​ተቀማጭነታቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ የአውሮፓ ኅብረት አባል አገራት እና ሌሎች የምዕራባውያን ዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላት፣ በትላንትናው ዕለት የተጠናቀቀውን 7ኛውን ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ አስመልክቶ የጋራ መግለጫ አውጥተዋል። አገራቱ በጋራ ባወጡት መግለጫ ኢትዮጵያ 7ተኛውን ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ ማካሄዷን...

ትላንት እስከ ምሽት ሁለት ሰዓት ድረስ 40 ሚሊዮን መራጮች ድምጽ መስጠታቸውን ምርጫ ቦርድ አስታወቀ

በትላንትናው ዕለት በተካሄደው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ፤ እስከ ምሽቱ ሁለት ሰዓት ድረስ 40 ሚሊዮን መራጮች ድምጽ መስጠታቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ ትላንት በሰጡት መግለጫ ተናገሩ። የምርጫ ቆጠራ በትላንትናው ዕለት በማይጠናቀቅባቸው ቦታዎች፤ በዛሬው...