የምርጫ አስፈፃሚዎች ክፍያቸው በመዘግየቱ “ራሳችንን ለእንግልት አሳልፈን ሰጥተናል” ሲሉ አማረሩ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቀጠራቸው ጊዜያዊ የምርጫ አስፈጻሚዎች ቀሪው 60 በመቶ ክፍያቸው እና የመራጮች ምዝገባ በተራዘመባቸው 14 ቀናት ሊታሰብላቸው የሚገባው ሙሉ አበል እንዳልተከፈላቸው በመግለጽ ቅሬታ አቀረቡ። ምርጫ ቦርድ በበኩሉ፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች ቀሪው ክፍያ እንዲፈጸምላቸው መጀመሪያ...
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ የታዋቂ ፖለቲከኞች የምርጫ...
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ7ኛውን ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ ውጤት የማረጋገጥ ሂደቱን በመቀጠል፣ የ723 የምርጫ ክልሎችን ውጤት ማፅደቁን ዛሬ ሰኔ 10 ቀን 2018 ዓ.ም. በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቀ።
ቦርዱ በ3 ዙር ካወጃቸው ውጤቶች በተጨማሪ ዛሬ የ40 የሕዝብ...
በአማራ ክልል በድምፅ መስጫው ዕለት በነዋሪዎች ምስክርነት እና በባለሥልጣናት መግለጫዎች መካከል መቃረን መፈጠሩ ተገለጠ
ግንቦት 24፣ 2018 ቀን 2018 ዓ.ም. በተካሄደው 7ኛው ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ በአማራ ክልል በሚገኙ አንዳንድ ዞኖችና ወረዳዎች ውስጥ የምርጫ ሂደቱ በጸጥታ ችግር ምክንያት ተቋርጦ የነበረ ቢሆንም፣ የመንግሥት የአካባቢ መዋቅሮች “ሂደቱ በስኬት ተጠናቋል” የሚል የግምገማ ውጤት...
ምርጫ ቦርድ የቁጫ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ያቀረበውን “የውጤት ይሰረዝልኝ” አቤቱታ ውድቅ አደረገ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቁጫ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቁሕዴፓ) በቁጫ ምርጫ ክልል የተካሄደው የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ውጤት እንዲሰረዝለት ያቀረበውን ይፋዊ አቤቱታ ውድቅ ማድረጉን አስታወቀ።
ቦርዱ ሰኔ 9 ቀን 2018 ዓ.ም. ለፓርቲው በጻፈውና የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ አቶ...
የምርጫ ዕለት በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች የተከሰተው ምንድን ነው?
ግንቦት 24፣ ቀን 2018 ዓ.ም. የተካሄደው የኢትዮጵያ 7ኛው ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ፣ በአንዳንድ የኦሮሚያ እና አማራ አካባቢዎች በፀጥታ መታወክ ሳቢያ 143 የምርጫ ጣቢያዎች ምርጫ ከጀመሩ በኋላ እንዲያቋርጡ መገደዳቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገልጾ ነበር። ይሁንና የተከሰተው...
በ25 ድምፅ ወደ ምክር ቤት፤ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ እጅግ ዝቅተኛ በሆነ የድምፅ ቁጥር የተመረጡ...
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከሰኔ 2 እስከ ሰኔ 4 ቀን 2018 ዓ.ም. ባወጣቸው ተከታታይ መግለጫዎች ያፀደቃቸው ከፊል ውጤቶች፣ በርካታ ተፎካካሪ በሌለባቸው የምርጫ ክልሎች የሚወዳደሩ ዕጩዎች እጅግ ዝቅተኛ በሆነ የመራጮች ድምፅ ወደ ምክር ቤቶች መግባታቸውን አሳዩ።
ቦርዱ...
ጎጎት ፓርቲ በስምንት የምርጫ ክልሎች መሠረታዊ የሕግ ጥሰት ተፈፅሟል አለ
የጎጎት ለጉራጌ አንድነት እና ፍትሕ ፓርቲ በጉራጌ ዞን እና በምሥራቅ ጉራጌ ዞኖች ስር በሚገነኑ ስምንት የምርጫ ክልሎች ላይ የምርጫውን ውጤት ፍጹም ሊያስቀይር የሚችል መሠረታዊ የሕግ ጥሰት መፈጸሙን አስታወቀ።
ፓርቲው ትናንት ሰኔ 4 ቀን 2018 ዓ.ም. ለጋዜጠኞች...
ብልፅግና ፓርቲ ያለተፎካካሪ የተወዳደረባቸውን በርካታ ወንበሮች ማሸነፉ ሲገለጽ፣ ተቃዋሚዎችም ብልፅግና ያልተወዳደረባቸውን ወንበሮች ማሸነፋቸውን ቀጥለዋል
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ7ኛውን ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ ከፊል ውጤት ማሳወቁን በመቀጠል፣ ዛሬ ሰኔ 4 ቀን 2018 ዓ.ም. በሰጠው 3ኛ ዙር መግለጫ የሌሎች 32 የምርጫ ክልሎችን ውጤት አፅድቆ ይፋ አድርጓል።
የቦርዱ የስነ-ዜጋ ትምህርት ኃላፊ አርማዬ አሰፋ...
ኦፌኮ ምርጫው “አምባገነናዊነትን ሕጋዊ ለማድረግ የተወጠነ የፖለቲካ ድራማ” ነው ሲል ከሰሰ
የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ትናንት ሰኔ 3 ቀን 2018 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ፣ በቅርቡ የተከናወነው 7ኛው ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ “በማግለል፣ በማስገደድ እና መዋቅራዊ በሆነ የምርጫ ስርቆት የተበከለ” በመሆኑ ሂደቱን ሙሉ በሙሉ ትርጉም አልባ አድርጎታል ሲል በከረረ...
እስካሁን በታወጁት የምርጫ ውጤቶች ብልፅግና ፓርቲ የተወዳደረባቸውን ወንበሮች በሙሉ ማሸነፉ ታውቋል
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ7ኛውን ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ ከፊል ውጤት እወጃ ከትላንት በመቀጠል፣ ዛሬ ሰኔ 3 ቀን 2018 ዓ.ም. ምሽት በስካይ ላይት ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የሌሎች 22 የምርጫ ክልሎችን ውጤት አፅድቆ ይፋ አድርጓል።
ቦርዱ ባወጣው...










