ምርጫ ቦርድ የቁጫ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ያቀረበውን “የውጤት ይሰረዝልኝ” አቤቱታ ውድቅ አደረገ

​የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቁጫ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቁሕዴፓ) በቁጫ ምርጫ ክልል የተካሄደው የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ውጤት እንዲሰረዝለት ያቀረበውን ይፋዊ አቤቱታ ውድቅ ማድረጉን አስታወቀ።  ቦርዱ ሰኔ 9 ቀን 2018 ዓ.ም.  ለፓርቲው በጻፈውና የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ አቶ...

የምርጫ ዕለት በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች የተከሰተው ምንድን ነው?

ግንቦት 24፣ ቀን 2018 ዓ.ም. የተካሄደው የኢትዮጵያ 7ኛው ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ፣ በአንዳንድ የኦሮሚያ እና አማራ አካባቢዎች በፀጥታ መታወክ ሳቢያ 143 የምርጫ ጣቢያዎች ምርጫ ከጀመሩ በኋላ እንዲያቋርጡ መገደዳቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገልጾ ነበር። ይሁንና የተከሰተው...

በ25 ድምፅ ወደ ምክር ቤት፤ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ እጅግ ዝቅተኛ በሆነ የድምፅ ቁጥር የተመረጡ...

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከሰኔ 2 እስከ ሰኔ 4 ቀን 2018 ዓ.ም. ባወጣቸው ተከታታይ መግለጫዎች ያፀደቃቸው ከፊል ውጤቶች፣ በርካታ ተፎካካሪ በሌለባቸው የምርጫ ክልሎች የሚወዳደሩ ዕጩዎች እጅግ ዝቅተኛ በሆነ የመራጮች ድምፅ ወደ ምክር ቤቶች መግባታቸውን አሳዩ። ቦርዱ...

ጎጎት ፓርቲ በስምንት የምርጫ ክልሎች መሠረታዊ የሕግ ጥሰት ተፈፅሟል አለ

የጎጎት ለጉራጌ አንድነት እና ፍትሕ ፓርቲ በጉራጌ ዞን እና በምሥራቅ ጉራጌ ዞኖች ስር በሚገነኑ ስምንት የምርጫ ክልሎች ላይ የምርጫውን ውጤት ፍጹም ሊያስቀይር የሚችል መሠረታዊ የሕግ ጥሰት መፈጸሙን አስታወቀ። ፓርቲው ትናንት ሰኔ 4 ቀን 2018 ዓ.ም. ለጋዜጠኞች...

ብልፅግና ፓርቲ ያለተፎካካሪ የተወዳደረባቸውን በርካታ ወንበሮች ማሸነፉ ሲገለጽ፣ ተቃዋሚዎችም ብልፅግና ያልተወዳደረባቸውን ወንበሮች ማሸነፋቸውን ቀጥለዋል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ7ኛውን ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ ከፊል ውጤት ማሳወቁን በመቀጠል፣ ዛሬ ሰኔ 4 ቀን 2018 ዓ.ም. በሰጠው 3ኛ ዙር መግለጫ የሌሎች 32 የምርጫ ክልሎችን ውጤት አፅድቆ ይፋ አድርጓል። የቦርዱ የስነ-ዜጋ ትምህርት ኃላፊ አርማዬ አሰፋ...

ኦፌኮ ምርጫው “አምባገነናዊነትን ሕጋዊ ለማድረግ የተወጠነ የፖለቲካ ድራማ” ነው ሲል ከሰሰ

የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ትናንት ሰኔ 3 ቀን 2018 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ፣ በቅርቡ የተከናወነው 7ኛው ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ “በማግለል፣ በማስገደድ እና መዋቅራዊ በሆነ የምርጫ ስርቆት የተበከለ” በመሆኑ ሂደቱን ሙሉ በሙሉ ትርጉም አልባ አድርጎታል ሲል በከረረ...

እስካሁን በታወጁት የምርጫ ውጤቶች ብልፅግና ፓርቲ የተወዳደረባቸውን ወንበሮች በሙሉ ማሸነፉ ታውቋል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ7ኛውን ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ ከፊል ውጤት እወጃ ከትላንት በመቀጠል፣ ዛሬ ሰኔ 3 ቀን 2018 ዓ.ም. ምሽት በስካይ ላይት ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የሌሎች 22 የምርጫ ክልሎችን ውጤት አፅድቆ ይፋ አድርጓል። ቦርዱ ባወጣው...

ምርጫ ቦርድ የ24 ምርጫ ክልሎች ውጤቶችን አፀደቀ፤ ሁለት ብልፅግና ያልተፎካከራቸው የተቃዋሚ ፓርቲ ዕጩዎች መመረጣቸው...

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ፣ ሰኔ 2፣ 2018 የመጀመሪያ ዙር የ24 ምርጫ ክልሎችን ውጤት አፅድቆ ይፋ አድርጓል። ከተረጋገጡት ውጤቶች መካከል ከአንድ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) እና ከአንድ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት ወንበሮች በቀር፣...

በልዩ ሁኔታ በተቋቋሙ የምርጫ ጣቢያዎች ድምፅ የመስጠት ሂደት እየተከናወነ ነው፤ በተፈናቃይ መጠለያዎች የመራጮች መረጃ...

ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ከተከናወነው 7ኛው ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ ቀጥሎ፣ በልዩ ሁኔታ በወታደራዊ ካምፖች እና በተፈናቃይ መጠለያ ጣቢያዎች ለሚገኙ ዜጎች ዛሬ ሰኔ 2 ቀን እንዲካሄድ በተያዘው መርሃ-ግብር መሠረት ድምፅ የመስጠት ሂደት እየተከናወነ ይገኛል። ይሁን እንጂ...

ተቃዋሚ ፓርቲዎች ክምርጫው ዕለት ጀምሮ ለወከባ መጋለጣቸውን ገለጹ

የ7ኛው ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ የድምፅ አሰጣጥ መጠናቀቁን ተከትሎ፣ ከተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በኩል የሚሰነዘሩ ይፋዊ ወቀሳዎችና ክሶች ከመዋቅራዊ የምርጫ ማጭበርበር ባለፈ፣ ወደ ድኅረ ምርጫ እስራት፣ ድብደባና የታዛቢዎች ማደናቀፍ መሸጋገራቸውን ፓርቲዎቹ ለ“ምርጫ 2018 - ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገለጹ።...